Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 36:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የዔሳው ልጅ የረዑኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ናሐት አለቃ፥ ዘራሕ አለቃ፥ ሻማ አለቃ፥ ሚዛህ አለቃ፥ በኤዶም ምድር የረዑኤል ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እነዚህም የዔሳው ሚስት የባሴማት ልጆች ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የዔሳው ልጅ ራጉኤል ልጆች፦ አለቃ ናሖት፣ አለቃ ዛራ፣ አለቃ ሣማና አለቃ ሚዛህ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከራጉኤል የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጅ ነበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የዔሳው ልጅ የረዑኤል ነገድ አለቆች፦ ናሐት፥ ዘራሕ፥ ሻማና ሚዛ ሲሆኑ እነዚህ በኤዶም የረዑኤል ነገድ አለቆች ናቸው፤ እነርሱም ዔሳው ከሚስቱ ከባሴማት የወለዳቸው ናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የዔ​ሳው ልጅ የራ​ጉ​ኤል ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ ናሖት መስ​ፍን፥ ዛራ መስ​ፍን፥ ሲን መስ​ፍን፥ ሞዛህ መስ​ፍን፤ በኤ​ዶም ምድር የራ​ጉ​ኤል ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ እነ​ዚ​ህም የዔ​ሳው ሚስት የቤ​ሴ​ሞት ልጆች ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የዔሳው ልጅ የራጉኤል ልጆች እነዚህ ናቸው ናሖት አለቃ ዛራ አለቃ ሣማ አለቃ ሚዛህ እለልቃ በኤዶም ምድር የራጉኤል ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው እነዚህም የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጆች ናቸው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 36:17
6 交叉引用  

ዔሳውም አርባ ዓመት ሲሆነው የሒታውያዊ የብኤሪን ልጅ ዮዲትን፥ የሒታውያዊ የኤሎንን ልጅ ቤሴሞትንም ሚስቶች አድርጎ አገባ፥


የረዑኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፦ ናሐት፥ ዘራሕ፥ ሻማና ሚዛ፤ እነዚህም የዔሳው ሚስት ባሴማት ልጆች ናቸው።


ቆሬ አለቃ፥ ገዕታም አለቃ፥ አማሌቅ አለቃ፥ በኤዶም ምድር የኤልፋዝ አለቆች እነዚህ ናቸው፥ እነዚህ የዓዳ ልጆች ናቸው።


የዔሳው ሚስት የኦሆሊባማ ልጆች እነዚህ ናቸው፦ የዑሽ አለቃ፥ ያዕላም አለቃ፥ ቆሬ አለቃ፥ የዔሳው ሚስት የዓና ልጅ የኦሆሊባማ አለቆች እነዚህ ናቸው።


ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደች፥ ባሴማትም ራዑኤልን ወለደች፥


የራጉኤል ልጆች፤ ናሖት፥ ዛራ፥ ሣማ፥ ሚዛህ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告