Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 34:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ነፍሱም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈች፥ ልጅቱንም አፈቀራት፥ እርሷንም በአፍቅሮት አናገራት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ልቡ በያዕቆብ ልጅ በዲና ተማረከ፤ ልጅቷንም በጣም ወደዳት፤ በጣፈጠም አንደበት አናገራት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በውበቷ ተማርኮ እጅግ ወደዳት፤ እርስዋም እንድትወደው ለማድረግ በፍቅር ቃል አነጋገራት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ልቡ​ና​ውም በያ​ዕ​ቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነ​ደፈ፤ ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱ​ንም ወደ​ዳት፤ ልብ​ዋ​ንም ደስ በሚ​ያ​ሰ​ኛት ነገር ተና​ገ​ራት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ልቡናውም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈ ብላቴናይቱንም ወደዳት ልብዋንም ደስ በሚያስኛት ነገር ተናገራት።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 34:3
11 交叉引用  

የአገሩ ገዢ የሒዋዊው ሰው የኤሞር ልጅ ሴኬም አያት፥ ወሰዳትም ከእርሷም ጋር ተኛ፥ አስነወራትም።


ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፥ “ይህችን ልጅ አጋባኝ” አለው።


አሁንም አትፍሩ፥ እኔ እናንተንና ልጆቻችሁን እመግባችኋለሁ።” አጽናናቸውም ደስ አሰኛቸውም።


የሚጠሉህን ትወዳለህ፤ የሚወዱህን ትጠላለህ፤ የጦር አዛዦችህና ወታደሮቻቸው ለአንተ ምንህም እንዳልሆኑ ይኸው ዛሬ ግልጽ አድርገሃል፤ ዛሬ አቤሴሎም በሕይወት ኖሮ እኛ ሁላችን አልቀን ቢሆን ደስ እንደሚልህ በዛሬው ዕለት ለማየት በቅቻለሁ።


ሕዝቅያስም በጌታ አገልግሎት አስተዋዮች የነበሩትን ሌዋውያን ሁሉ ያበረታታ ነበር። የአንድነትንም መሥዋዕት እያቀረቡ፥ የአባቶቻቸውንም አምላክ እያመሰገኑ ለሰባት ቀን ለበዓሉ የተዘጋጀውን ማዕድ በሉ።


ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፤ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፥ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፥ ከጌታም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርሷ ጩኹ።


እርሷም፦ “ውሽሞቼ ለእኔ የሰጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለችውን ወይንዋንና በለስዋን አጠፋለሁ፤ ዱርም አደርገዋለሁ፥ የምድረ በዳም አራዊት ይበሉታል።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ አባብላታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳም አመጣታለሁ፥ ለልብዋም እናገራለሁ።


ባሏ ታርቆ ሊመልሳት ወደ እርሷ ሄደ፤ ሲሄድም አሽከሩንና ሁለት አህዮችን ይዞ ነበር፤ ሴቲቱም ወደ አባቷ ቤት አስገባችው፤ አባቷም ባየው ጊዜ በደስታ ተቀበለው።


ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንደገና አለቀሱ፥ ዖርፋም አማቷን ሳመች፥ ሩት ግን አማቷ ጋር ተጣበቀች።


ዳዊት ከሳኦል ጋር የሚያደርገውን ንግግር እንዳበቃ፤ የዮናታን ነፍስ ከዳዊት ነፍስ ጋር ተቆራኘች፤ እንደራሱም አድርጎ ወደደው።


跟着我们:

广告


广告