Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 33:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዓይኑን አንስቶም ሴቶችንና ልጆችን ባየ ጊዜ፥ “እነዚህ ምኖችህ ናቸው?” አለ። እርሱም፦ “እግዚአብሔር ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከዚያም ዔሳው ቀና ብሎ ሲመለከት ሴቶቹንና ልጆቹን አየ፤ እርሱም፣ “እነዚህ ዐብረውህ ያሉት እነማን ናቸው?” ብሎ ጠየቀው። ያዕቆብም መልሶ፣ “እነዚህማ እግዚአብሔር በቸርነቱ ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ዔሳው በዙሪያው ተመልክቶ ሴቶቹንና ልጆቹን ባየ ጊዜ “እነዚህ ሁሉ ከአንተ ጋር ያሉ ሰዎች የማን ናቸው?” አለ። ያዕቆብም “ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዔሳ​ውም ዐይ​ኑን አነ​ሣና ሴቶ​ች​ንና ልጆ​ችን አየ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነ​ዚህ ምኖ​ችህ ናቸው?” እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእኔ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ የሰ​ጠኝ ልጆች ናቸው” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዓይኑንም አነሣና ሴቶችንና ልጆችን አየ እንዲህም አለ፦ እነዚህ ምኖችህ ናቸው? እርሱም፦ እግዚአብሔር ለእኔ ለባሪያህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው አለ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 33:5
9 交叉引用  

ያዕቆብም ራሔልን ተቆጥቶ፦ በውኑ እኔ የሆድን ፍሬ በነሣሽ በእግዚአብሔር ቦታ ነኝን? አላት።


ከዚህ በኋላ ሴቶች ባርያዎችም ከልጆቻቸው ጋር ቀርበው እጅ ነሡ፥


ዮሴፍም ለአባቱ፦ “እግዚአብሔር በዚህ የሰጠኝ ልጆቼ ናቸው” አለ። እርሱም፦ “እባርካቸው ዘንድ ወደዚህ አቅርብልኝ” አለ።


ጌታም ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በጌታ መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ እንዲነግሥ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።


እነሆ፥ ልጆች የጌታ ስጦታ ናቸው፥ የማሕጸንም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው።


እነሆ፤ እኔና ጌታ የሰጠኝ ልጆች በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ለእስራኤል ምልክትና ድንቅ ነን።


እንዲሁም፥ “እኔ በእርሱ እታመናለሁ፤” ደግሞም “እነሆኝ እኔ፥ እግዚአብሔር የሰጠኝንም ልጆች” ይላል።


ቦዔዝም ሩትን ወሰደ፥ ሚስትም ሆነችው፥ ወደ እርሷም ገባ፤ እግዚአብሔርም ፅንስ ሰጣት፥ ወንድ ልጅም ወለደች።


ስለዚህ ሕፃን ጸለይሁ፤ ጌታም የለመንሁትን ሰጠኝ።


跟着我们:

广告


广告