ዘፍጥረት 30:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)40 ያዕቆብም ጠቦቶቹን ለየ፥ ሽመልመሌ መሳይና ጥቁር ያለባቸውን በጎቹንም ሁሉ በላባ በጎች ፊት ለፊት አኖረ፥ መንጎቹንም ለብቻቸው አቆማቸው፥ ወደ ላባም በጎች አልጨመራቸውም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም40 ያዕቆብ ግልገሎቹን ለብቻ ለያቸው፤ የቀሩትንም የላባ መንጎች ሽመልመሌና ጥቋቍር በሆኑት በጎች ትይዩ አቆማቸው፤ በዚህም መሠረት የራሱ መንጋ ከላባ መንጋ ጋራ እንዳይቀላቀል ለብቻ ለየ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም40 ያዕቆብ እነዚህን ግልገሎች ለብቻ ለየ፤ የቀሩትን ግን ዝንጒርጒርና ጥቊር በሆኑት በላባ መንጋዎች ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በዚህ ዐይነት የራሱን መንጋ ወደ ላባ መንጋ ሳይቀላቅል ለብቻ አቆማቸው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)40 ያዕቆብም ተባት በጎችንና እንስት በጎችን ለይቶ ነጭና ሐመደ ክቦ በሆኑ አውራዎች ፊት አቆማቸው፤ መንጎቹንም ለብቻቸው አቆማቸው። ከላባ በጎች ጋርም አልጨመራቸውም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)40 ያዕቆብም ጠቦቶቹን ለየ፥ ሽመልመሌ መሳይና ጥቁር ያለባቸውን በጎቹንም ለብቻቸው አቆማቸው፥ ወደ ላባም በጎች አልጨመራቸውም። 参见章节 |