Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 28:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሥቶ ወደ ካራን ሄደ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ያዕቆብ ቤርሳቤህን ትቶ ወደ ካራን ለመሄድ ተነሣ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ያዕ​ቆ​ብም ከአ​ዘ​ቅተ መሐላ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 28:10
14 交叉引用  

ታራም ልጁን አብራምን፥ የልጅ ልጁን የሐራንን ልጅ ሎጥንና የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሣራን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ዑር ወጡ፥ ወደ ካራንም መጡ፥ ከዚያም ተቀመጡ።


አብራምም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ሄደ፥ ሎጥም ከእርሱ ጋር ሄደ፥ አብራምም ከካራን በወጣ ጊዜ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበረ።


አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ፥ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ።


ከዚያም ወደ ቤርሳቤህ ወጣ።


አሁንም ልጄ ሆይ ቃሌን ስማ፥ ተነሣና ወደ ካራን ምድር ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሂድ፥


ያዕቆብም፦ “ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንት የወዴት ናችሁ?” አላቸው። እነርሱም፦ “እኛ የካራን ነን” አሉት።


ለባርያህ ካሳየኸው ከጽኑ ፍቅርና ከታማኝነትህ ሁሉ ትንሽ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፥ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበር፥ አሁን ግን ለሁለት ወገን የተከፈልኩ ሆንሁ።


እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው፦ “ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ፥ በዚያም ኑር፥ ከወንድምህ ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ ለእግዚአብሔርም መሠውያውን ሥራ።”


በዚያም መሠዊያውን ሠራ፥ የዚያንም ቦታ ስም “ኤልቤቴል” ብሎ ጠራው፥ እርሱ ከወንድሙ ፊት በሸሸበት ጊዜ እግዚአብሔር በዚያ ተገልጦለት ነበርና።


እስራኤልም ያለውን ሁሉ ይዞ ተነሣ፥ ወደ ቤርሳቤህ ደረሰ፥ መሥዋዕትንም ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ ሠዋ።


ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ሂድ፥ አንተ ከግብጽ ምድር ካወጣኸው ሕዝብ ጋር ከዚህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ‘ለዘርህ እሰጣታለሁ’ ብዬ ወደ ማልሁባት ምድር ውጣ፤


ኃጢአት በገለዓድ አለ፤ ፈጽመው ከንቱ ናቸው፤ በሬዎችን በጌልገላ ይሠዋሉ፥ መሠዊያዎቻቸውም በእርሻ ትልሞች ላይ የድንጋይ ክምር ይሆናሉ።


ከጥቂት ቀንም በኋላ ንጉሡ አግሪጳ በርኒቄም ለፊስጦስ ሰላምታ እንዲያቀርቡ ወደ ቂሳርያ ወረዱ።


እርሱም እንዲህ አለ “ወንድሞችና አባቶች ሆይ! ስሙ። የክብር አምላክ ለአባታችን ለአብርሃም በካራን ሳይቀመጥ ገና በመስጴጦምያ ሳለ ታየና


跟着我们:

广告


广告