Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 27:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ምናልባት አባቴ ቢዳስሰኝ በፊቱ እንደሚዘብት እሆናለሁ፥ መርገምንም በላዬ አመጣለሁ፥ በረከትን አይደለም።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ታዲያ፣ አባቴ ቢዳስሰኝ እንዳታለልሁት ያውቃል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ፣ በምርቃት ፈንታ ርግማን አተርፋለሁ ማለት ነው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ምናልባት አባቴ ቢዳስሰኝና እንዳታለልኩት ቢያውቅ በምርቃት ፈንታ ርግማን እንደማተርፍ ታውቂ የለምን?” አላት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ምና​ል​ባት አባቴ ቢዳ​ስ​ሰኝ በፊቱ እን​ደ​ም​ን​ቀው እሆ​ና​ለሁ፤ መር​ገ​ምን በላዬ አመ​ጣ​ለሁ፤ በረ​ከ​ት​ንም አይ​ደ​ለም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በፊቱ እንደሚዘብት እሆናለሁ መርገምንም በላዬ አመጣለሂ በረከትን አይደለም።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 27:12
11 交叉引用  

ልጆቹም ባደጉ ጊዜ፥ ዔሳውም በዱር የሚውል ብልኅ አዳኝ ሆነ፥ ያዕቆብ ግን ጭምት ሰው ነበረ፥ በቤትም ይቀመጥ ነበር።


እርሱም እንዲህ አለ፦ “በእውነት ስሙ ያዕቆብ ተባለ፥ ሁለት ጊዜ አሰናክሎኛልና፥ ብኩርናዬን ወሰደ፥ አሁንም እነሆ በረከቴን ወሰደ። ደግሞም፦ ለእኔ በረከትን አላስቀረህልኝምን?” አለ።


የወንድምህ ቁጣ ከአንተ እስኪመለስ ድረስ፥ ያደረግህበትንም እስኪረሳው ድረስ፥ ከዚያም ልኬ አስመጣሃለሁ፥ በአንድ ቀን ሁለታችሁን ለምን አጣለሁ?”


እንዲህም አለ፦ “ከነዓን የተረገመ ይሁን! ለወንድሞቹም የባርያዎች ባርያ ይሁን።”


ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፥ የሚስተውና የሚያስተው የእርሱ ናቸው።


የጌታን ሥራ በቸልታ የሚያደርግ ርጉም ይሁን፥ ደም ከማፍሰስም ሰይፉን የሚከለክል ርጉም ይሁን።


“በመንጋው ውስጥ ተባዕት እያለው ለጌታ ተስሎት እያለ ነውር ያለበትን የሚሠዋ ተንኮለኛ ሰው የተረገመ ነው። እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “ስሜም በሕዝቦች መካከል የተፈራ ነውና።”


በክብርና በውርደት፥ በመመስገንና በመሰደብ ኖረናል። አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤


“‘ዐይነ ስውሩን በተሳሳተ መንገድ የሚመራ፥ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።


ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ።


跟着我们:

广告


广告