Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 24:48 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

48 በግምባሬም አጎነበስሁ፥ ለእግዚአብሔርም ሰገድሁ፥ የጌታዬን የወንድሙን ልጅ ለልጁ እወስድ ዘንድ በቀና መንገድ የመራኝን የጌታዬን የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

48 ተደፍቼም ለእግዚአብሔር ሰገድሁ፤ ለጌታዬ ወንድም የልጅ ልጅ የሆነችውን ቈንጆ፣ ለጌታዬ ልጅ እንዳገኝለት በቀና መንገድ የመራኝን የጌታዬ የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

48 ከዚህ በኋላ ለጌታዬ ልጅ ሚስት የምትሆነዋን ሴት ወዳገኘሁበት ወደ ጌታዬ ወንድም ቤት በቀና መንገድ ለመራኝ ለእግዚአብሔር በጒልበቴ ተንበርክኬ ሰገድሁ፤ የጌታዬን የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንኩ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

48 ይህ​ንም ነገር ከአ​ን​ደ​በቷ በሰ​ማሁ ጊዜ እጅግ ደስ አሰ​ኘ​ችኝ። ለጆ​ሮ​ዎ​ች​ዋም ጉት​ቻ​ዎ​ችን ለእ​ጆ​ች​ዋም አም​ባ​ሮ​ችን አድ​ርጌ አስ​ጌ​ጥ​ኋት። ደስ ባሰ​ኘ​ች​ኝም ጊዜ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገ​ድሁ፤ የጌ​ታ​ዬን የወ​ን​ድ​ሙን ልጅ ለልጁ እወ​ስድ ዘንድ በቀና መን​ገድ የመ​ራ​ኝን የጌ​ታ​ዬን የአ​ብ​ር​ሃ​ምን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ንሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

48 በግምባሬም አጎነበስሁ፥ ለእግዚአብሔርም ሰገድሁ፤ የጌታዬን የወንድሙን ልጅ ለልጁ እወስድ ዘንድ በቀና መንገድ የመራኝን የጌታዬን የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንሁ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 24:48
11 交叉引用  

በቱኤል ርብቃን ወለደ፤ ሚልካ እነዚህን ስምንት ልጆች ለአብርሃም ወንድም ለናኮር ወለደችለት።


የአብርሃምም ሎሌ ነገራቸውን በሰማ ጊዜ ወደ ምድር ወድቆ ለእግዚአብሔር ሰገደ።


በአምላካችን ፊት ራሳችንን ዝቅ እንድናደርግ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንድንለምን በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ።


ወደሚኖሩበት ከተማ ይሄዱ ዘንድ በቀና መንገድን መራቸው።


አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፥ ዐይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።


በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ፥ ቅጥሮችዋን መርምሩ፥ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ።


ሥርዓቱንና ሕጉን አስተምራቸው፥ የሚሄዱበትን መንገድና የሚያደርጉትን ሥራ አሳውቃቸው።


የጥበብን መንገድ አስተማርሁህ፥ በቀናች ጎዳና መራሁህ።


ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ አምላክህ ጌታ ነኝ።


跟着我们:

广告


广告