Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 14:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 አብራምም ጠላቶቹን ለማጥቃት አገልጋዮቹን በቡድን ከፋፍሎ በሌሊት እርሱ ከባርያዎቹ ጋር ወረደባቸው፥ መታቸውም፥ በደማስቆ ግራ እስካለችውም እስከ ሖባ ድረስ አሳደዳቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አብራም ጠላቶቹን ለማጥቃት ሰራዊቱን ሌሊቱን በቡድን በቡድን ከፋፍሎ ከደማስቆ በስተሰሜን እስከሚገኘው እስከ ሖባ ድረስ አሳደዳቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እዚያ ሰዎቹን በቡድን ከፋፍሎ እርሱና አገልጋዮቹ ከጠላቶቹ ጋር በሌሊት ጦርነት ገጥመው ድል አደረጋቸው፤ ከደማስቆ በስተሰሜን እስከሚገኘው እስከ ሖባ ድረስ አሳደዳቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እር​ሱም ከብ​ላ​ቴ​ኖቹ ጋር በሌ​ሊት ደረ​ሰ​ባ​ቸው፤ መታ​ቸ​ውም፤ በደ​ማ​ስቆ ግራ እስ​ካ​ለ​ች​ውም እስከ ሖባ ድረስ አሳ​ደ​ዳ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ብላቴኖቹንም ከፍሎ በሌሊት እርሱ ከባሪያዎቹ ጋር ወረደባቸው፥ መታቸውም፥ በደማስቆ ግራ እስካለችውም እስከ ሖባ ድረስ አሳደዳቸው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 14:15
14 交叉引用  

አብራምም፦ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ ምንን ትሰጠኛለህ? እኔም ያለ ልጅ እሄዳለሁ፥ የቤቴም መጋቢ የደማስቆ ሰው ይህ ኤልዔዘር ነው አለ።


በዚህም ምክንያት ንጉሥ አሳ በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ የተረፈውን ወርቅና ብር ሁሉ በማውጣት በባለሟሎቹ እጅ፥ በደማስቆ ከተማ ለነበረው የጣብሪሞን ልጅ፥ የሔዝዮን የልጅ ልጅ ለሆነው ለሶርያ ንጉሥ ቤንሀዳድ ስጦታ አድርጎ ላከለት፤ ከስጦታውም ጋር እንዲህ የሚል መልእክት ነበረ፤


ቸር ሰው ይራራል ያበድራልም፥ ነገሩንም በቀና መንገድ ይፈጽማል።


ስለ ደማስቆ የተነገረ ትንቢት። እነሆ፥ ደማስቆ ከተማነቷ ይቀራል፤ የፍርስራሽም ክምር ትሆናለች።


የሶርያ ራስ ደማስቆ፤ የደማስቆ ራስ ረአሶን ነውና፤ በሥልሳ አምስት ዓመት ውስጥ፤ የኤፍሬም ሕዝብ ይበታተናል፤ ሕዝብ መሆኑም ይቀራል።


ስለ ደማስቆ፤ ክፉ ወሬ ሰምተዋልና ሐማትና አርፋድ አፈሩ ቀለጡም፤ ለማረፍም እንደማይችል ባሕር በፍርሃት ተናወጡ።


በሁሉም ነገር ሀብታም ስለ ነበርሽ፥ ከንብረትሽ ብዛት የተነሣ፥ ደማስቆ በሔልቦን የወይን ጠጅ፥ ነጭ የበግ ጠጉር፥ ነጋዴሽ ነበረች።


ሐማት፥ ቤሮታ፥ በደማስቆ ድንበርና በሐማት ድንበር መካከል ያለው ሲብራይም፥ በሐውራን ድንበር አጠገብ ያለው ሐጸርሃቲኮን፥


በደማስቆም ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀመዝሙር ነበረ፤ ጌታም በራእይ “ሐናንያ ሆይ!” አለው። እርሱም “ጌታ ሆይ! እነሆኝ፤” አለ።


በዚህ መንገድ ያሉትንም ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ቢያገኝ፥ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች ደብዳቤ ከእርሱ ለመነ።


ሳውልም ከምድር ተነሣ፤ ዐይኖቹም በተከፈቱ ጊዜ ምንም አላየም፤ እጁንም ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አገቡት።


አፈጻጸሙም የሚከተለው ነው፦ አበዳሪ ሁሉ ለባልጀራውም ያበደረውን ይተዋል፥ ጌታ የዕዳ ምሕረት አውጆአልና፥ ያበደረውን ከባልንጀራው ወይም ከወንድሙ ዕዳውን እንዲከፍለው አይጠይቀው።


ሦስቱን መቶ ሰዎች በሦስት ቡድን ከፍሎ፥ እያንዳንዱን ሰው ቀንደ መለከትና በውስጡ ችቦ ያለበት ባዶ ማሰሮ በእጁ እንዲይዝ አደረገ።


跟着我们:

广告


广告