Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ገላትያ 5:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የተገረዘ ሰው ሁሉ ሕግን በሙሉ የመፈጸም ግዴታ አለበት ብዬ ደግሜ እመሰክራለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 መገረዝ ለሚፈልግ ሁሉ ሕግን በሙሉ የመፈጸም ግዴታ እንዳለበት እንደ ገና ለእያንዳንዱ በግልጽ እናገራለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “መገረዝ ያስፈልገኛል” ብሎ የሚገረዝ ሁሉ “ሕግን በሙሉ የመፈጸም ግዴታ አለበት” ብዬ እንደገና አስጠነቅቀዋለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ደግ​ሞም ለተ​ገ​ዘረ ሰው ሁሉ የኦ​ሪ​ትን ሕግ መፈ​ጸም እን​ደ​ሚ​ገ​ባው እመ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሕግንም ሁሉ እንዲፈጽም ግድ አለበት ብዬ ለሚገረዙት ሁሉ ለእያንዳንዶች ደግሜ እመሰክራለሁ።

参见章节 复制




ገላትያ 5:3
19 交叉引用  

ነገሥታቶቻችንም አለቆቻችንም ካህናቶቻችንም አባቶቻችንም ሕግህን አልጠበቁም፥ የመሰከርህባቸውንም ትእዛዝህንና ምስክርህን አልሰሙህም።


“እናንተ ዕውራን መሪዎች ‘ማንም በቤተ መቅደስ ቢምል ምንም አይደለም፥ ማንም በቤተ መቅደስ ወርቅ ቢምል ግን በመሐላው ይያዛል፤’ የምትሉ ወዮላችሁ።


ደግሞም ‘ማንም በመሠዊያው ቢምል ምንም አይደለም፤ ማንም በላዩ ላይ ባለው መባ ቢምል ግን በመሐላው ይያዛል፤’ ትላላችሁ።


አምስት ወንድሞች አሉኝና፤ እነርሱ ደግሞ ወደዚህ ሥቃይ ስፍራ እንዳይመጡ ይመስክርላቸው’ አለ።


አንዳንዶችም ከይሁዳ ወረዱና “እንደ ሙሴ ሥርዓት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም፤” ብለው ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር።


በብዙ ሌላ ቃልም መሰከረና “ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ፤” ብሎ መከራቸው።


አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ አስጠነቀቅኋቸው።


ሕግን የምትፈጽም ከሆነ መገረዝ ይጠቅማል፤ ሕግን የምትተላለፍ ከሆነ ግን መገረዝህ እንደ አለመገረዝ ሆኖአል።


ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ ከርግማን በታች ናቸው፤ “በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ የማይኖርና የማይፈጽማቸው ሁሉ የተረገመ ይሁን፤” ተብሎ ተጽፎአልና።


እነሆ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ፥ ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም።


በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ በክርስቶስ ኢየሱስ መገረዝ ወይም አለመገረዝ አይጠቅምም።


እንግዲህ አሕዛብ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ፥ በጌታም እለምናችኋለሁ።


“‘የዚህን ሕግ ቃሎች በመፈጸም የማይጸና የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።”


ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር በደረሰባቸው ጊዜ ይህ መዝሙር ምስክር ይሆንባቸዋል። በዘራቸው የሚረሳ አይደለምና። ወደ ማልሁላቸው ምድር ሳላስገ ባቸው በፊት ምን ለማድረግ እንደሚያስቡ እንኳን አስቀድሜ ዐውቃለሁ።”


ጌታ አምላክህንም ብትረሳና፥ ባዕዳን አማልክት ብትከተል ብታመልካቸውም ብትሰግድላቸውም፥ ፈጽሞ እንደምትጠፉ ዛሬውኑ አበክሬ አስጠነቅቅሃለሁ።


አስቀድመን ደግሞ እንደ ነገርናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።


አብ ወልድን የዓለም አዳኝ እንዲሆን እንደ ላከው አይተናል፥ እንመሰክራለንም።


跟着我们:

广告


广告