ገላትያ 4:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 እንግዲህ መባረካችሁ የት አለ? ቢቻል ኖሮ ዐይኖቻችሁን እንኳ አውጥታችሁ ትሰጡኝ እንደ ነበረ እኔ እመሰክርላችኋለሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ለመሆኑ ያ ሁሉ ደስታችሁ የት ደረሰ? ቢቻላችሁ ዐይናችሁን ቢሆን እንኳ አውጥታችሁ የምትሰጡኝ እንደ ነበራችሁ እመሰክራለሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ከዚህ በፊት የነበራችሁ ደስታ ሁሉ የት ሄደ? ቢቻልስ ዐይኖቻችሁን እንኳ አውጥታችሁ ትሰጡኝ እንደ ነበረ እኔ ራሴ እመሰክርላችኋለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 አሁንስ ደስ ማሰኘታችሁ ወዴት አለ? ቢቻላችሁስ ዐይናችሁንም እንኳ ቢሆን አውጥታችሁ ትሰጡኝ እንደ ነበረ፥ እኔ ምስክራችሁ ነኝ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 እንግዲህ ደስ ማሰኘታችሁ ወዴት አለ? ቢቻልስ ዓይኖቻችሁን አውጥታችሁ በሰጣችሁኝ ብዬ እመሰክርላችኋለሁ። 参见章节 |