ገላትያ 3:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ወንድሞች ሆይ! እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። የጸና ኪዳን፥ የሰው ስንኳ ቢሆን፥ ማንም አያፈርሰውም ወይም አይጨምርበትም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ወንድሞች ሆይ፤ ከሰው ዕለታዊ ሕይወት የተለመደውን ምሳሌ አድርጌ ላቅርብ፤ የሰው ኪዳን እንኳ አንድ ጊዜ ከጸደቀ በኋላ ማንም ሊሽረው ወይም በርሱ ላይ ሊጨምርበት እንደማይችል ሁሉ፣ በዚህም ጕዳይ ቢሆን እንደዚሁ ነው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ወንድሞቼ ሆይ! እስቲ ይህን ነገር በሰው ዘንድ ከተለመደ ነገር ጋር አነጻጽሩት፤ አንድ ሰው የገባው ቃል ኪዳን እንኳ ከጸደቀ በኋላ ማንም ሰው ሊሽረው ወይም ሊጨምርበት አይችልም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ሰው ልማድ እንናገራለን፤ ሰውም እንኳን የጸናውን ኪዳን አይንቅም አይጨምርበትምም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። የሰው ስንኳ ቢሆን እርግጠኛውን ኪዳን ማንም አይንቅም ወይም አይጨምርበትም። 参见章节 |