Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ገላትያ 2:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጴጥሮስን ለተገረዙት ሐዋርያ እንዳደረገው፥ እኔንም ደግሞ ለአሕዛብ ሐዋርያ አድርጎኛል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ጴጥሮስን ለአይሁድ ሐዋርያ እንዲሆን የሠራ እግዚአብሔር፣ በእኔ የአሕዛብ ሐዋርያዊ አገልግሎትም ሠርቷል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ስለዚህ ጴጥሮስን የአይሁድ ሐዋርያ ሆኖ እንዲያገለግል ያደረገው አምላክ እኔንም የአሕዛብ ሐዋርያ ሆኜ እንዳገለግል አድርጎኛል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ወደ ተገ​ዘሩ አይ​ሁድ በተ​ላከ ጊዜ ጴጥ​ሮ​ስን የረ​ዳው እርሱ እኔ​ንም ባል​ተ​ገ​ዘሩ አሕ​ዛብ ዘንድ ረዳኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ለተገረዙት ሐዋርያ እንዲሆን ለጴጥሮስ የሠራለት፥ ለእኔ ደግሞ ለአሕዛብ ሐዋርያ እንድሆን ሠርቶአልና።

参见章节 复制




ገላትያ 2:8
23 交叉引用  

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ፤” አለ።


ሕዝቡም ሁሉ ዝም አሉ፤ በርናባስና ጳውሎስም እግዚአብሔር በእጃቸው በአሕዛብ መካከል ያደረገውን ምልክትና ድንቅ ሁሉ ሲተርኩላቸው ይሰሙ ነበር።


ይህም ጳውሎስ ‘በእጅ የተሠሩቱ አማልክት አይደሉም፤’ ብሎ፥ በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን ከጥቂት ክፍል በቀር በእስያ ሁሉ ብዙ ሕዝብን እንደ አስረዳና እንደ አሳተ አይታችኋል፤ ሰምታችሁማል።


ሰላምታም ካቀረበላቸው በኋላ በእርሱ ማገልገል እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ያደረገውን በእያንዳንዱ ተረከላቸው።


እርሱም ‘ሂድ፤ እኔ ወደ አሕዛብ ከዚህ ወደ ሩቅ እልክሃለሁና፤’ አለኝ።”


ነገር ግን ቃሉን ከሰሙት ብዙዎች አመኑ፥ የወንዶችም ቍጥር አምስት ሺህ ያህል ሆነ።


በዚያን ጊዜ እጃቸውን ጫኑባቸው፤ መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ።


ጌታም “ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤


ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን የሆንሁትን ሆኛለሁ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋ ከንቱ አልሆነም፤ ይልቁን ከሁሉም በላይ በትጋት ሠርቻለሁ፤ ሆኖም ግን እኔ ሳልሆን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው።


የሐዋርያነቴ ማኅተም በጌታ እናንተ ናችሁና፥ ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን ለእናንተስ ምንም ቢሆን ሐዋርያ ነኝ።


እንግዲህ መንፈስን የሚሰጣችሁ በእናንተም ድንቅን የሚሠራ፥ በሕግ ሥራ ነውን? ወይስ በእምነት በመስማታችሁ ነው?


ለዚህም ነገር ደግሞ፥ በእኔ ውስጥ በኃይል በሚያቀጣጥለው ጉልበት ሁሉ እየተጋደልሁ እደክማለሁ።


ስለዚህም የመልእክትን ቃል፥ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል ከእኛ በተቀበላችሁ ጊዜ፥ በእውነት እንዳለ በእናንተ በአማኞች ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት፥ እኛ ደግሞ እግዚአብሔርን ሳናቋርጥ እናመሰግናለን።


跟着我们:

广告


广告