Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ገላትያ 2:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የእግዚአብሔርን ጸጋ አልናቅሁም፤ ጽድቅ በሕግ በኩል የሚገኝ ከሆነ እንግዲያውስ ክርስቶስ የሞተው በከንቱ ነው ማለት ነዋ!

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የእግዚአብሔርን ጸጋ አላቃልልም፤ ጽድቅ በሕግ በኩል የሚገኝ ከሆነማ፣ ክርስቶስ እንዲያው በከንቱ ሞተ ማለት ነዋ!”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ አላስቀርም፤ ሰው የሚጸድቀው ሕግን በመፈጸም ከሆነ ክርስቶስ የሞተው በከንቱ ነው ማለት ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጸጋ አል​ክ​ድም፤ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት የሚ​ጸ​ድቁ ከሆነ እን​ኪ​ያስ ክር​ስ​ቶስ በከ​ንቱ ሞተ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።

参见章节 复制




ገላትያ 2:21
16 交叉引用  

ጌታ የአሕዛብን ምክር ያጠፋል፥ የአሕዛብንም አሳብ ይመልሳል።


እኔ ግን፦ “በከንቱ ደከምሁ፥ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ጉልበቴን ፈጀሁ፤ ፍርዴ ግን በጌታ ዘንድ፥ ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው” አልኩ።


“እናንተስ፦ ‘ጥበበኞች ነን የጌታንም ሕግ ከእኛ ጋር ነው’ እንዴት ትላላችሁ? እነሆ፥ በውኑ የጸሐፊዎች ሐሰተኛ ብዕር ሐሰት አድርጎታል።


ደግሞም፥ እንዲህ አላቸው፤ “የራሳችሁን ወግ ለመጠበቅ ስትሉ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የምትተውበት ዘዴ።


የእግዚአብሔርን ጽድቅ ባለማወቅ፥ የራሳቸውንም ጽድቅ ለመመሥረት በመፈለግ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም።


በጸጋ ከሆነ ግን በሥራ መሆኑ ቀርቶአል፤ ያለዚያ ጸጋ ጸጋ መሆኑ ቀርቶአል።


ስለ ኃጢአታችን ለሞት ተላልፎ ተሰጠ፤ ለጽድቃችንም ተነሣ።


እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?


ክርስቶስም ካልተነሣ ስብከታችን ዋጋ ቢስ ነው፤ እምነታችሁም ከንቱ ነው።


ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ነው፤ እናንተም እስከ አሁን ድረስ ከነኀጢአታችሁ አላችሁ ማለት ነው።


የሰበክሁላችሁን ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ፥ ያመናችሁት በከንቱ ካልሆነ በስተቀር፥ የምትድኑበትን ወንጌል ነው።


ሆኖም ሰው የሚጸድቀው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ በሕግ ሥራ እንዳልሆነ አውቀን፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ በማመን እንድንጸድቅ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል። ሥጋ ሁሉ በሕግ ሥራ አይጸድቅም።


ይህን ያፈረስኩትን እንደገና የማንጽ ከሆንሁ፥ እኔ ራሴ ሕግ ተላላፊ ነኝ።


እንግዲህ ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ይቃወማልን? በጭራሽ አይደለም። ሕይወትን ሊሰጥ የሚችል ሕግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ በእርግጥ ጽድቅ በሕግ በኩል በሆነ ነበር፤


እንግዲህ በሌዊ ክህነት ፍጹምነት የተገኘ ከሆነ፥ ሕዝቡ በዚያ ላይ የተመሠረተን ሕግ ተቀብለዋልና፤ ወደ ፊት እንደ አሮን ሹመት የሚቆጠር ሳይሆን፥ እንደ መልከጼዴቅ ሹመት የሆነ ሌላ ካህን ሊነሣ ስለምን ያስፈልጋል?


跟着我们:

广告


广告