Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 5:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ወደ ይሁዳ አገር ወደ ታላቁ አምላክ ቤትም እንደ ሄድን በንጉሡ ዘንድ ይታወቅ፥ እርሱም በትልቅ ድንጋይ ተሠራ፥ በቅጥሩም ውስጥ እንጨት ተደረገ፥ ያም ሥራ በጥንቃቄ ይሠራል፥ በእጃቸውም ይከናወናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የታላቁ አምላክ ቤተ መቅደስ ወደሚገኝበት ወደ ይሁዳ አውራጃ ሄደን እንደ ነበር በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን በታላላቅ ድንጋዮች እየገነቡና ቅጥሩንም በወፍራም ምሰሶዎች እየሠሩ ነው፤ ሥራው በትጋት በመከናወንና በእነርሱም አመራር በመፋጠን ላይ ይገኛል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ወደ ይሁዳ ምድር ሄደን የታላቁ አምላክ ቤተ መቅደስ በድንጋይና በጠርብ እንጨት ሲሠራ ማየታችን ለግርማዊነትዎ የታወቀ ይሁን፤ ሥራውም በሽማግሌዎቹ መሪነት በጥንቃቄና በፍጥነት እየተሠራ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ወደ ይሁዳ ሀገር ወደ ታላ​ቁም አም​ላክ ቤት እንደ ሄድን ንጉሡ ይወቅ፤ እር​ሱም በጥሩ ድን​ጋይ ይሠ​ራል፤ በቅ​ጥ​ሩም ውስጥ ልዩ እን​ጨት ይደ​ረ​ጋል፤ ያም ሥራ በት​ጋት ይሠ​ራል፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም ይከ​ና​ወ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ወደ ይሁዳ አገር ወደ ታላቁም አምላክ ቤት እንደ ሄድን ንጉሡ ይወቅ፤ እርሱም በትልቅ ድንጋይ ተሠራ፤ በቅጥሩም ውስጥ እንጨት ተደረገ፤ ያም ሥራ በትጋት ይሠራል፤ በእጃቸውም ይከናወናል።

参见章节 复制




ዕዝራ 5:8
20 交叉引用  

የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።


እንዲህም የሚል ደብዳቤ ላኩለት፦ “ለንጉሡ ዳርዮስ ሙሉ ሰላም ይሁን፤


እኛም ሽማግሌዎቹን፦ ‘ይህን ቤት እንድትሠሩ፥ ይህንንም ቅጥር እንድታድሱ ማን አዘዛችሁ?’ ብለን ጠየቅናቸው።


ይህም ለሰማያት አምላክ መልካም መዓዛ እንዲያቀርቡ፥ ለንጉሥና ለልጆቹ ሕይወትም እንዲጸልዩ ነው።


በሦስት መደዳ ታላላቅ ድንጋይ፥ አንድ መደዳ እንጨት ይደረግ፤ ወጪውም ከንጉሡ ቤት ይሰጥ።


በንጉሡና በልጆቹ መንግሥት ላይ ቁጣ እንዳይሆን፥ የሰማያት አምላክ የሚያዘው ሁሉ ልክ እንዳዘዘው ለሰማያት አምላክ ቤት ይደረግ።


በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የአውራጃው መሪዎች እነዚህ ናቸው፤ እስራኤል፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች እያንዳንዱ በየርስቱና በየከተማቸው በይሁዳ ከተሞች ኖሩ።


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ ገዛ ከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።


ጌታ ታላቅ ነው እጅግም የተመሰገነ ነው፥ ታላቅነቱም የማይመረመር ነው።


ምክንያቱም ጌታ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፥ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ፥ ኃያልም፥ የሚያስፈራም፥ በፍርድ የማያደላ፥ ጉቦም የማይቀበል ነው።


ጠላቶቻችን እንኳ እንደሚስማሙበት፥ ዓለታቸው እንደ እኛ ዓለት አይደለም።


跟着我们:

广告


广告