Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 9:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የእስራኤልም አምላክ ክብር በላዩ ላይ አርፎ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መግቢያ ሄዶ ነበር፥ በፍታ የለበሰውን በወገቡም የጸሐፊ ቀለም ቀንድ የያዘውን ሰው ጠራ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በዚህ ጊዜ የእስራኤል አምላክ ክብር ከነበረበት ከኪሩብ በላይ ተነሥቶ ወደ ቤተ መቅደሱ መድረክ ሄደ። እግዚአብሔርም በፍታ የለበሰውን በጐኑም የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር ያነገበውን ሰው ጠራ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከዚህ በኋላ የእስራኤልን አምላክ ክብር የሚገልጥ ነጸብራቅ ቀድሞ ካረፈበት ከኪሩብ ላይ ተነሥቶ ወደ ቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ሄደ፤ እግዚአብሔርም በፍታ የለበሰውንና የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር የያዘውን ሰው፥ ጠራው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ክብር በበ​ላዩ ከነ​በ​ረ​በት ኪሩብ ተነ​ሥቶ ወደ ቤቱ መድ​ረክ ሄዶ ነበር፤ በፍ​ታም የለ​በ​ሰ​ውን፥ የሰ​ን​ፔር መታ​ጠ​ቂ​ያም በወ​ገቡ የታ​ጠ​ቀ​ውን ሰው ጠራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የእስራኤልም አምላክ ክብር በበላዩ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መድረክ ሄዶ ነበር፥ በፍታ የለበሰውን የጸሐፊውንም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘውን ሰው ጠራ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 9:3
6 交叉引用  

የጌታ ክብርም ከኪሩቤል ወጥቶ በቤቱ መግቢያ ላይ ቆመ፥ ቤቱም በደመናው ተሞላ፥ አደባባዩም በጌታ የክብር ብርሃን ተሞላ።


እኔም ተነሥቼ ወደ ሜዳው ወጣሁ፥ እነሆ በዚያ በኮቦር ወንዝ ያየሁትን ክብር የሚመስል የጌታ ክብር ቆሞ ነበር፥ በግምባሬም ተደፋሁ።


እነሆ በዚያ በሜዳው እንዳየሁት ራእይ የሚመስል የእስራኤል አምላክ ክብር ነበረ።


እነሆ ስድስት ሰዎች ወደ ሰሜን ከሚመለከተው ከላይኛው በር መንገድ መጡ፥ እያንዳንዱም አጥፊውን መሣሪያ በእጁ ይዞ ነበር፥ በመካከላቸውም የበፍታ ልብስ የለበሰ፥ የጸሐፊ የቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘ አንድ ሰው ነበረ። እነርሱም ገብተው በናሱ መሠዊያ አጠገብ ቆሙ።


跟着我们:

广告


广告