ሕዝቅኤል 48:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ለጌታ የተቀደሰ ስለሆነ ከእርሱ ምንም አይሸጡም አይለውጡም፥ የምድሪቱንም በኵራት ወደ ሌላ አይተላለፍም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ከዚህ ላይ መሸጥ ወይም መለወጥ የለባቸውም። ይህ ከምድሪቱ ሁሉ ምርጥ ስለ ሆነ፣ ወደ ሌላ እጅ አይተላለፍም፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነውና። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ለእግዚአብሔር የሚከለለው ስፍራ በምድሪቱ ከሚገኘው ሁሉ የተሻለ ምርጥ ቦታ ነው፤ ከእርሱም ተከፍሎ የሚሸጥና የሚለወጥ ወይም ለማንም በውርስ የሚተላለፍ አይሆንም፤ እርሱ ለእግዚአብሔር ተለይቶ የተቀደሰ ስፍራ ነው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ነውና ከእርሱ ምንም አይሸጡም፤ አይለውጡምም፤ የምድሩም ቀዳምያት አይፋለስም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ነውና ከእርሱ ምንም አይሸጡም አይለውጡምም፥ የምድሩም በኵራት አይፋለስም። 参见章节 |