Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 47:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የደቡቡም ድንበር ከታማር ጀምሮ እስከ ሜርባ ቃዴስ ውኃ፥ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ይሆናል። ይህም የደቡቡ ድንበር ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በደቡብ በኩል ወሰኑ ከታማር ይነሣና እስከ መሪባ ቃዴስ ውሃ ይደርሳል፤ ከዚያም የግብጽን ደረቅ ወንዝ ተከትሎ እስከ ታላቁ ባሕር ይዘልቃል፤ ይህ የደቡቡ ወሰን ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “የደቡቡም ድንበር ከታማር ተነሥቶ እስከ መሪባ ቃዴስ ድረስ፥ ከዚያም ከግብጽ ሸለቆ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ይደርሳል፤ ይህም የደቡብ ድንበር ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የደ​ቡ​ቡም ድን​በር ከታ​ማር ጀምሮ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብፅ ወንዝ እስከ ታላቁ ባሕር ይሆ​ናል። የደ​ቡ​ቡም ድን​በር ይህ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የደቡብም ድንበር ከታማር ጀምሮ እስከ ሜርባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብጽ ወንዝ እስከ ታላቁ ባህር ድረስ ይሆናል። የደቡቡ ድንበር ይህ ነው።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 47:19
15 交叉引用  

በዚያም በቤተ መቅደሱ ሰሎሞንና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰባት ቀን ሙሉ የዳስ በዓል አክብረው ሰነበቱ፤ በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ካለው ምድር ሁሉ የመጣው ሕዝብ እጅግ ብዙ ነበር።


ባዕላት፥ በይሁዳ በረሓማ አገር የምትገኝ ታማር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች እንደገና ሠራ።


ሰዎችም መጥተው እንዲህ በማለት ለኢዮሣፍጥ አወሩለት፦ “ከባሕሩ ማዶ ከሶሪያ ታላቅ ሠራዊት መጥቶብሃል፤ እነሆም፥ ዐይን-ጋዲ በተባለች በሐሴሶን ታማር ይገኛሉ።”


ጫንቃውን ከሸክም፥ እጆቹንም በቅርጫት ከመገዛት አራቅሁ።


በዚያ ቀን ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ እስከ ግብጽ ደረቅ ወንዝ ጌታ እህሉን ይወቃል፥ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።


ከዔንጌዲ ጀምሮ እስከ ዔንዔግላይም ድረስ አጥማጆች በዚያ ይቆማሉ፤ የመረቦች መዘርጊያ ይሆናል፤ ዓሣዎችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣ በየወገናቸው እጅግ ይበዛሉ።


የምድሪቱ ድንበር ይህ ነው፤ በሰሜኑ ወገን ከታላቁ ባሕር ጀምሮ በሔትሎን መንገድ ወደ ጼዳድ መግቢያ፥


ከጋድ ድንበር ቀጥሎ በደቡብ በኩል ድንበሩ ከታማር ጀምሮ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብጽ ወንዝ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ይሆናል።


የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በመጀመሪያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝቡም በቃዴስ ተቀመጡ፤ ማርያምም በዚያ ሞተች፥ በዚያም ተቀበረች።


የእስራኤል ልጆች ከጌታ ጋር የተጣሉበት፥ እርሱም በመካከላቸው ቅዱስ መሆኑን የገለጠበት ይህ የመሪባ ውኃ ነው።


የደቡቡ ወገን ከጺን ምድረ በዳ ተነሥቶ የኤዶምያስን ዳርቻ እያዋሰነ የሚያልፈው ይሆናል፤ የደቡቡም ድንበራችሁ ከጨው ባሕር ዳር በምሥራቅ በኩል ይጀምራል፤


ድንበሩም ከዓጽሞን ወደ ግብጽ ወንዝ ይዞራል፥ ባሕሩም ማብቂያው ይሆናል።


ምክንያቱም ሁለታችሁም በጺን ምድረ በዳ፥ በቃዴስ በመሪባ ውሃ አጠገብ በእኔ ላይ መታመናችሁን በእስራኤላውያን ፊት ስላጐደላችሁና ቅድስናዬንም በእስራኤላውያን መካከል ስላላከበራችሁ ነው።


ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦ “ማሳህ በተባለው ቦታ ለፈተንኸው፥ በመሪባ ውኃም ለተከራከርኸው፥ ቱሚምህን ለሌዊ ስጠው፥ ኡሪምህም ለዚህ ቅዱስ ሰው ነው፤


በምሥራቅም በኩል ያለውን ዓረባ እስከ ኪኔሬት ባሕር ድረስ፥ በቤትየሺሞት መንገድ አጠገብ እስካለው እስከ ዓረባ ባሕር እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ በደቡብም በኩል ከፈስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለውን ምድር ነበር፤


跟着我们:

广告


广告