Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 46:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እንዲህም አለኝ፦ “ካህናቱ ሕዝቡን ለመቀደስ ወደ ውጭው አደባባይ እንዳያወጡ የበደሉን መሥዋዕትና የኃጢአቱን መሥዋዕት የሚቀቅሉበት፥ የእህሉንም ቁርባን የሚጋግሩበት ስፍራ ይህ ነው።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እርሱም፣ “ይህ ስፍራ ሕዝቡን ለመቀደስ መሥዋዕቱን ወደ ውጩ አደባባይ እንዳያወጡ፣ ካህናቱ የበደሉን መሥዋዕትና የኀጢአቱን መሥዋዕት የሚቀቅሉበት፣ የእህሉንም ቍርባን የሚጋግሩበት ቦታ ነው” አለኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ ቦታ ካህናቱ ለኃጢአትና ለበደል ማስተስረያ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበውን ሥጋ የሚቀቅሉበትና የእህል መሥዋዕት የሚጋግሩበት ክፍል ነው፤ በዚህም ዐይነት በሕዝቡ ላይ ጒዳት እንዳይደርስ ከተቀደሰው መሥዋዕት ሁሉ ወደ ውጪው አደባባይ አይወጣም።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “ካህ​ናቱ ሕዝ​ቡን ለመ​ቀ​ደስ ወደ ውጭው አደ​ባ​ባይ እን​ዳ​ይ​ወጡ የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​በ​ስ​ሉ​በት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን የሚ​ጋ​ግ​ሩ​በት ስፍራ ይህ ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እርሱም፦ ካህናቱ ሕዝቡን ለመቀደስ ወደ ውጭው አደባባይ እንዳያወጡ የበደሉን መሥዋዕትና የኃጢአቱን መሥዋዕት የሚቀቅሉበት፥ የእህሉንም ቍርባን የሚጋግሩበት ስፍራ ይህ ነው አለኝ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 46:20
13 交叉引用  

የፋሲካውንም መሥዋዕት እንደ ሥርዓቱ በእሳት ጠበሱ፤ የተቀደሰውንም ቁርባን በምንቸትና በሰታቴ በድስትም ቀቀሉ፥ ለሕዝቡም ሁሉ በፍጥነት አደረሱ።


ለክህነት ሥርዓት የቀረበውን አውራ በግ ወስደህ ሥጋውን በተቀደሰ ስፍራ ትቀቅለዋለህ።


ወደ ውጭው አደባባይ ወደ ሕዝቡ በሚወጡበት ጊዜ ያገለገሉበትን ልብሳቸውን ያውልቁ፥ በተቀደሰው ቤት ውስጥ ያኑሩት፥ ሕዝቡንም በልብሳቸው እንዳይቀድሱ ሌላ ልብስ ይልበሱ።


የእህሉን ቁርባን፥ የኃጢአትን መሥዋዕትና የበደልን መሥዋዕት ይበላሉ፤ በእስራኤልም እርም የሆነው ነገር ሁሉ ለእነርሱ ይሆናል።


ወደ ውጭው አደባባይ አወጣኝ በአደባባይም ወዳለው ወደ አራቱ ማዕዘን አዞረኝ፤ እነሆ በእያንዳንዱ የአደባባይ ማዕዘን አደባባይ ነበረ።


እንዲህም አለኝ፦ “እነዚህ የቤቱ አገልጋዮች የሕዝቡን መሥዋዕት የሚቀቅሉባቸው ስፍራዎች ናቸው።”


“ማናቸውም ሰው የእህል ቁርባን ለጌታ ሲያቀርብ ቁርባኑ ከመልካም ዱቄት ይሁን፤ ዘይትም ያፈስበታል፥ ዕጣንም ይጨምርበታል፤


ከእህሉም ቁርባን የተረፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ይህም ለጌታ በእሳት ከቀረበው የቁርባን ክፍል በመሆኑ እጅግ የተቀደሰ ነው።


ከእህሉም ቁርባን የተረፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ይህም ለጌታ በእሳት ከቀረበው የቁርባን ክፍል በመሆኑ እጅግ የተቀደሰ ነው።


በዚያ ቀን በፈረሶች ሻኩራ ላይ፦ “ለጌታ የተቀደሰ” ተብሎ ይጻፋል። በጌታም ቤት ያሉ ምንቸቶች በመሠዊያው ፊት እንዳሉ ዳካዎች ይሆናሉ።


跟着我们:

广告


广告