Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 46:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በበዓላትና በክብረ በዓል ቀኖች የእህሉ ቁርባን ለወይፈኑ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለአውራ በጉ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለጠቦቶቹም እጁ የሰጠችውን ያህል፥ ለኢፍ መስፈሪያም አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ይሆናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በበዓላትና በተወሰኑት በዓላት፣ ከወይፈኑ ጋራ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፣ ከአውራ በጉም ጋራ አንድ የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቍርባን ያቅርብ፤ ከበግ ጠቦቶቹ ጋራ የሚያቀርበው የእህል ቍርባን ግን ሰውየው የወደደውን ያህል ይሁን፤ እያንዳንዱም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የሂን መስፈሪያ ዘይት ይኑረው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በታላላቅና በታናናሽ በዓላት ቀኖች ከእያንዳንዱ ኰርማና ከእያንዳንዱ የበግ አውራ ጋር የሚቀርበው የኽህል መባ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ይሁን፤ ለእግዚአብሔር የሚሰግደው ሰው ከእያንዳንዱ የበግ ጠቦት ጋር የፈቀደውን ያኽል ያቅርብ። ከእያንዳንዱም የኢፍ መስፈሪያ መባ ጋር ሦስት ሊትር የወይራ ዘይት አብሮ ይቅረብ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በበ​ዓ​ላ​ትና በክ​ብረ በዓል ቀኖች የእ​ህሉ ቍር​ባን ለወ​ይ​ፈኑ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለአ​ውራ በጉ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም እጁ እን​ደ​ሚ​ች​ለው ያህል፥ ለአ​ንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዱቄት አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በበዓላትና በክብረ በዓል ቀኖች የእህሉ ቍርባን ለወይፈኑ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለአውራ በጉ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለጠቦቶቹም እንደሚቻለው ያህል፥ ለኢፍ መስፈሪያም አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ይሆናል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 46:11
8 交叉引用  

በየበዓላቱ፥ በየመባቻው፥ በየሰንበታቱ፥ በእስራኤል ቤት ዓመት በዓል ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን፥ የመጠጡን መሥዋዕት ማቅረብ በመስፍኑ ላይ ይሆናል፤ እርሱ ለእስራኤል ቤት ሊያስተሰርይ የኃጢአቱን መሥዋዕትና ስጦታውን፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሰላሙን መሥዋዕት ያቀርባል።


ለአንድ ወይፈን አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለአንድ አውራ በግ አንድ የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቁርባን፥ ለአንድ የኢፍ መስፈሪያ አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ያቅርብ።


ለአውራ በጉ አንድ የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቁርባን ይሁን፥ ለእያንዳንዱም ጠቦት እጁ የሰጠችውን ያህል የእህል ቁርባን ይሁን፥ ለአንዱም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ያቅርብ።


ለወይፈኑ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ለአውራው በግ አንድ የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቁርባን ያቅርብ፥ ለጠቦቶቹም እጁ የቻለችውን ያህል፥ ለአንዱም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ያቅርብ።


跟着我们:

广告


广告