Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 45:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ዐሥር ሺህ ክንድ የሆነ ስፍራ ለቤቱ አገልጋዮች ለሌዋውያን ይሆናል፥ ሃያ ቤቶችም ለእነርሱ ርስት ይሆናሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ ወርዱ ዐሥር ሺሕ ክንድ ስፋት ያለው ስፍራ መኖሪያ ከተሞቻቸውን እንዲከትሙ በቤተ መቅደስ ለሚያገለግሉ ሌዋውያን ርስት ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ቀሪው አጋማሽ ማለትም ርዝመቱ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱ ዐሥር ሺህ ክንድ የሆነው ቦታ ደግሞ በቤተ መቅደስ ለሌሎች ልዩ ልዩ አገልግሎት ለተመደቡት ሌዋውያን ርስት ይሆናል፤ ለእነርሱ መኖሪያ የሚሆኑ ከተሞችም በዚያ ይሠራሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ርዝ​መ​ቱም ሃያ አም​ስት ሺህ፥ ወር​ዱም ዐሥር ሺህ የሆነ ስፍራ ለቤቱ አገ​ል​ጋ​ዮች ለሌ​ዋ​ው​ያን መኖ​ሪያ ርስት ከሃያ ዕቃ ቤቶች ጋር ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ርዝመቱም ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም አሥር ሺህ የሆነ ዕፍራ ለቤቱ አገልጋዮች ለሌዋውያን ይሆናል፥ ለሚቀመጡባቸውም ከተሞች ለራሳቸውም የርስት ይዞታ ይሆናል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 45:5
9 交叉引用  

ከዚያም ወደ ውጪው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆ በአደባባዩ ዙሪያ የተሠሩ ዕቃ ቤቶችና ወለል ነበሩ፤ በወለሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።


ይህም ለካህናቱ የተቀደሰ መባ ይሆናል፤ በሰሜን በኩል ሀያ አምስት ሺህ፥ በምዕራብ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በምሥራቅ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በደቡብ በኩል ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል። የጌታ መቅደስም በመካከሉ ይሆናል።


ለሌዋውያኑ በካህናቱ ድንበር አጠገብ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ዐሥር ሺህ ይሆናል፥ ርዝመቱ ሁሉ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆናል።


መባው ሁሉ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል፤ የተቀደሰውን መባ ከከተማይቱ ድርሻ ጋር አራት ማዕዘን አድርጋችሁ ትሰጣላችሁ።


ሰባት ቀን በዳሶች ውስጥ ትቀመጣላችሁ፤ በእስራኤል ያሉት የአገሩ ተወላጆች ሁሉ በዳሶች ውስጥ ይቀመጣሉ፤


“ሌዋውያን የሚቀመጡባቸውን ከተሞች ከርስታቸው እንዲሰጡ የእስራኤልን ልጆች እዘዛቸው፤ በከተሞቹም ዙሪያ ያለውን መሰማሪያ ለሌዋውያን ስጡ።


跟着我们:

广告


广告