ሕዝቅኤል 45:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ርስት አድርጋችሁ ምድሪቱን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ከምድሪቱ የተቀደሰውን ክፍል መባ አድርጋችሁ ወደ ጌታ ታቀርባላችሁ። ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል፤ በዳርቻው ዙሪያ ሁሉ የተቀደሰ ይሆናል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 “ ‘ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ በዕጣ በምትከፋፈሉበት ጊዜ፣ ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ሺሕ ክንድ የሆነውን አንዱን ክፍል፣ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ስፍራ አድርጋችሁ ስጡ፤ ስፍራውም በሙሉ ቅዱስ ይሆናል፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ምድሪቱ ለእያንዳንዱ ነገድ በርስትነት በምትከፋፈልበት ጊዜ አንድ ዕጣ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል፤ እርሱም ርዝመቱ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ፥ ወርዱም ኻያ ሺህ ክንድ ይሆናል፤ ጠቅላላውም ክልል የተቀደሰ ይሆናል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 “ርስትም አድርጋችሁ ምድርን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ከምድር የተቀደሰውን የዕጣ ክፍል መባ አድርጋችሁ ወደ እግዚአብሔር ታቀርባላችሁ። ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ፥ ወርዱም ሃያ ሺህ ክንድ ይሆናል፤ በዳርቻው ሁሉ ዙሪያው የተቀደሰ ይሆናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ርስትም አድርጋችሁ ምድርን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ከምድር የተቀደሰውን የዕጣ ክፍል መባ አድርጋችሁ ወደ እግዚአብሔር ታቀርባላችሁ። ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል፥ በዳርቻው ሁሉ ዙሪያውን የተቀደሰ ይሆናል። 参见章节 |