Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 44:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ጌታም እንዲህ አለኝ፦ ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል፤ አይከፈትምም፥ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ይህ በር እንደ ተዘጋ ይኖራል፤ መከፈት የለበትም፤ ማንም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና፤ ተዘግቶ ይኖራል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ በር እንደ ተዘጋ ይኖራል እንጂ ከቶ አይከፈትም፤ የእስራኤል አምላክ እኔ እግዚአብሔር የገባሁበት ስለ ሆነ፥ ማንም በዚህ በር መጠቀም አይችልም፤ ስለዚህም እንደ ተዘጋ ይኖራል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ይህች በር ተዘ​ግታ ትኖ​ራ​ለች እንጂ አት​ከ​ፈ​ትም፤ ሰውም አይ​ገ​ባ​ባ​ትም፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገብ​ቶ​ባ​ታ​ልና ተዘ​ግታ ትኖ​ራ​ለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እግዚአብሔርም፦ ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 44:2
5 交叉引用  

የእስራኤልንም አምላክ አዩ፤ ከእግሩም በታች እንደ ሰማያት የጠራ እንደ ብሩህ ሰንፔር ድንጋይ የሚመስል ወለል ነበረ።


ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በር አመጣኝ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጠኛው አደባባይ ፊቱ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር በስድስቱ የሥራ ቀኖች ይዘጋ፤ ነገር ግን በሰንበት ቀን ይከፈት እንዲሁም በወር መባቻ ቀን ይከፈት።


跟着我们:

广告


广告