Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 44:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በራሳቸው ላይ የተልባ እግር መጠምጠሚያ ይሁን፥ በወገባቸውም ላይ የተልባ እግር ሱሪ ይሁን፤ የሚያልብ ነገር አይታጠቁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በራሳቸው ላይ ከበፍታ ፈትል የተሠራ ጥምጥም ያድርጉ፤ እንዲሁም ከበፍታ ፈትል የተሠራ ሱሪ በወገባቸው ላይ ይታጠቁ፤ እንዲያልባቸው የሚያደርግ ማንኛውንም ልብስ አይልበሱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በራሳቸው ላይ ከበፍታ የተሠራ መጠምጠሚያ ይጠምጥሙ፤ በወገባቸውም ከበፍታ የተሠራ የውስጥ ልብስ ይልበሱ፤ ማናቸውም ላብ የሚያመጣ መታጠቂያ አይታጠቁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በራ​ሳ​ቸው ላይ የተ​ልባ እግር መጠ​ም​ጠ​ሚያ ይሁን፤ በወ​ገ​ባ​ቸ​ውም ላይ የተ​ልባ እግር ሱሪ ይሁን፤ የሚ​ያ​ልብ ነገር አይ​ታ​ጠቁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በራሳቸው ላይ የተልባ እግር መጠምጠሚያ ይሁን፥ በወገባቸውም ላይ የተልባ እግር ሱሪ ይሁን፥ የሚያወዛም ነገር አይታጠቁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 44:18
9 交叉引用  

ከጥሩ በፍታ መጠምጠሚያውን፥ ከጥሩ በፍታም ቆቦች፥ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ ሱሪዎችን ሠሩ፥


የራስ መሸፈኛውን፤ ዐልቦውን፤ ሻሹን፤ የሽቶ ብልቃጡን፤ አሸን ክታቡን፤


ለንጉሡና ለንጉሥ እናት ለእቴጌይቱ፦ “የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ተዋርዳችሁ ተቀመጡ” በል።


በዝምታ ተክዝ፥ ለሙታን አታልቅስ፤ መጠምጠሚያህን በራስህ ላይ አድርግ፥ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፤ ከንፈርህን አትሸፍን፥ የዕዝን እንጀራም አትብላ።


መጠምጠሚያችሁ በራሳችሁ ላይ፥ ጫማችሁም በእግራችሁ ይሆናል፤ ዋይ አትሉም ወይም አታለቅሱም፤ በኃጢአታችሁ ትመነምናላችሁ፥ እርስ በእርሳችሁም ታለቅሳላችሁ።


የተቀደሰውን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፥ የበፍታውም ሱሪ በገላው ላይ ይሁን፥ በመርገፍም የተጌጠውን የበፍታው መታጠቂያ ይታጠቅ፥ የበፍታውንም መጠምጠሚያ ይጠምጥም፤ እነዚህ የተቀደሱ ልብሶች ናቸው፤ ገላውንም በውኃ ታጥቦ ይልበሳቸው።


ነገር ግን ሁሉም በአግባብና በሥርዓት ይሁን።


跟着我们:

广告


广告