ሕዝቅኤል 44:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 በመቅደሴ ውስጥ አገልጋዮች፥ በቤቱም በሮች ዘበኞች ይሆናሉ፥ በቤቱም ውስጥ ያገለግላሉ፤ ለሕዝቡም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና መሥዋዕትን ያርዳሉ፥ ሊያገለግሉአቸውም በፊታቸው ይቆማሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 የቤተ መቅደሱ በር ኀላፊ በመሆንና በርሱም ውስጥ በማገልገል፣ መቅደሴን ሊያገለግሉ ይችላሉ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ዐርደው ስለ ሕዝቡ ሊሠዉ፣ በፊታቸው ሊቆሙና ሊያገለግሏቸው ይችላሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 እነርሱ በቤተ መቅደሱ በር ጠባቂነት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሰዎች የሚያቀርቡአቸውን መሥዋዕቶች በማረድ፥ እንዲሁም ሰዎችን በማገልገል እንዲሠሩ ይፈቅድላቸዋል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ነገር ግን በመቅደሴ ውስጥ አገልጋዮች ይሆናሉ፤ በቤቱም በሮች በረኞች ይሆናሉ፤ በቤቱም ውስጥ ያገለግላሉ፤ ለሕዝቡም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕትን ይሠዋሉ፤ ያገለግሉአቸውም ዘንድ በፊታቸው ይቆማሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ነገር ግን በመቅደሴ ውስጥ አገልጋዮች ይሆናሉ፥ በቤቱም በሮች በረኞች ይሆናሉ በቤቱም ውስጥ ያገለግላሉ፥ ለሕዝቡም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕቱን ያርዳሉ፥ ያገለግሉአቸውም ዘንድ በፊታቸው ይቆማሉ። 参见章节 |