ሕዝቅኤል 43:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 የመሠዊያውም ልክ በክንድ ይህ ነው፤ ክንዱም አንድ ክንድ ከስንዝር ነው። መሠረቱ ቁመቱ አንድ ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ ነው፥ ዙሪያውም አንድ ስንዝር ጠርዝ አለው፤ ይህም የመሠዊያው ከፍታ ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም13 “የመሠዊያው ልክ በረዥም ክንድ ይህ ነው፤ ይኸውም ክንድ ከስንዝር ማለት ነው፤ ቦዩ አንድ ክንድ ጥልቀት፣ አንድ ክንድ ወርድ ያለው ሲሆን፣ ዙሪያው አንድ ስንዝር ጠርዝ አለው፤ የመሠዊያውም ከፍታ ይህ ነው፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 የመሠዊያውም ልክ እንደሚከተለው ነው፦ መሠዊያው ያረፈበት አንድ ረጅም ክንድ ርዝመትና አንድ ረጅም ክንድ ወርድ ሲሆን የዙሪያ ጠርዙም ስፋት አንድ ስንዝር ነው፤ ይህም ረጅም ክንድ በሌላው አንድ ክንድ ከጋት ይሆናል፤ ይህም የመሠዊያው ከፍታ ነው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 የመሠዊያው ልክ በክንድ ይህ ነው፤ ክንዱም ክንድ ተጋት ነው። የመሠረቱም ቁመቱ አንድ ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ ነው፤ አንድ ስንዝርም ክፈፍ ዳር ዳሩን በዙሪያው አለ፤ የመሠዊያው ቁመት እንዲሁ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 የመሠዊያውም ልክ በክንድ ይህ ነው ክንዱም ክንድ ተጋት ነው። የመሠረቱም ቁመቱ አንድ ክንድ ወርዱም አንድ ክንድ ነው፥ አንድ ስንዝርም ክፈፍ ዳር ዳሩን በዙሪያው አለ፥ የመሠዊያው መሠረት እንዲሁ ነው። 参见章节 |