ሕዝቅኤል 42:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ካህናቱም ከገቡ በኋላ የሚያገለግሉበትን ልብስ ሳያወልቁ ከመቅደሱ ወደ ውጭው አደባባይ አይወጡም፥ የተቀደሱ ናቸውና፤ ወደ ሕዝቡ ቦታ ሲቀርቡ ሌላ ልብስ መልበስ አለባቸው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ካህናቱ አንድ ጊዜ ወደ ተቀደሰው ቦታ ከገቡ በኋላ፣ ያገለገሉበትን ልብስ ሳያወልቁ ወደ ውጩ አደባባይ መውጣት አይችሉም፤ የተቀደሰ ነውና፤ ወደ ሕዝቡ ቦታ ከመምጣታቸው በፊት ሌላውን ልብሳቸውን መልበስ አለባቸው።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ካህናቱ ወደተቀደሰው ቦታ ገብተው የሚያገለግሉባቸውን ልብሶች ከለበሱ በኋላ ያን ያገልግሎት ልብስ ሳያወልቁ ወደ ውጪው አደባባይ አይወጡም፤ ልብሶቹም የተቀደሱ ስለ ሆኑ ከተቀደሰው ቦታ ወጥተው ለሕዝብ ወደተፈቀደው ቦታ ከመድረሳቸው በፊት ሌላ ልብስ መልበስ ይኖርባቸዋል።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ካህናቱም በገቡ ጊዜ ከመቅደሱ በውጭው አደባባይ አይወጡም፤ የሚያገለግሉበትን ልብሳቸውን ግን ቅዱስ ነውና በዚያ ያኖሩታል፤ ሌላም ልብስ ለብሰው ወደ ሕዝብ ይወጣሉ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ካህናቱም በገቡ ጊዜ ከመቅደሱ በውጭው አደባባይ አይወጡም፥ የሚያገለግሉበትን ልብሳቸውን ግን ቅዱስ ነውና በዚያ ያኖሩታል፥ ሌላም ልብስ ለብሰው ወደ ሕዝብ ይወጣሉ። 参见章节 |