ሕዝቅኤል 42:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 በፊታቸው የነበረው መንገድም በሰሜን በኩል ያሉትን ክፍሎች ይመስል ነበር። ርዝመታቸውም፥ ወርዳቸውም፥ መውጫቸውም አቀማመጣቸውና መግቢያዎቻቸውም ተመሳሳይ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ከፊት ለፊታቸውም መተላለፊያ መንገድ አለ። እነዚህ በሰሜን በኩል ካሉት ክፍሎች ጋራ ተመሳሳይ ሲሆኑ፣ ርዝመትና ወርዳቸው፣ መውጫና መጠናቸው አንድ ዐይነት ነበር፤ በሰሜን በኩል እንዳሉት በሮች፣ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 በክፍሎቹም ፊት ለፊት መተላለፊያ ነበር፤ ክፍሎቹ ልክ በሰሜን በኩል እንዳሉት ክፍሎች ርዝመትና ወርዳቸው፥ መውጫዎቻቸውና የበሮቻቸው አቀማመጥ ተመሳሳይ ነበር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 በስተፊታቸውም የነበረ መንገድ በሰሜን በኩል እንደ ነበረው እንደ ዕቃ ቤቶቹ መንገድ አምሳል ነበር። ርዝመታቸውም፥ ወርዳቸውም፥ መውጫቸውም፥ ሥርዐታቸውም፥ መዝጊያዎቻቸውም በዚያው ልክ ነበሩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 በስተ ፊታቸውም የነበረ መንገድ በሰሜን በኩል እንደ ነበረው እንደ ዕቃ ቤቶቹ መንገድ ምስያ ነበረ። ርዝመታቸውም ወርዳቸውም መውጫቸውም ሥርዓታቸውም መዝጊያዎቻቸውም በዚያው ልክ ነበረ። 参见章节 |