Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 41:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የሰው ፊት በአንድ ወገን ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ይመለከት ነበር፥ የአንበሳ ፊት ደግሞ በሌላው ወገን ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ይመለከት ነበር፤ በቤቱ ሁሉ ዙሪያ እንደዚህ ተቀርጾ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የሰው ፊት ያለው ኪሩብ በአንድ በኩል ወዳለው ዘንባባ የዞረ ሲሆን፣ የአንበሳ ፊት ያለውም በሌላ በኩል ወዳለው ዘንባባ ዞሮ ነበር። ሁሉም በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ላይ ተቀርጸው ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በአንድ በኩል የሰው ፊት ቅርጽ ያለው ወደ ዘንባባው ሲመለከት፥ በሌላም አቅጣጫ የደቦል አንበሳ ቅርጽ ያለው ወደ ዘንባባው ዛፍ ይመለከት ነበር። እነርሱም በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ተቀርጸው ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በአ​ንድ ወገን ወደ አለው የዘ​ን​ባባ ዛፍ የሰው ፊት ይመ​ለ​ከት ነበር፤ በሌ​ላ​ውም ወገን ወደ አለው ዘን​ባባ የአ​ን​በሳ ፊት ይመ​ለ​ከት ነበር፤ በቤቱ ሁሉ ዙሪያ እን​ደ​ዚህ ተቀ​ርጾ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በአንድ ወገን ወዳለው የዘንባባ ዛፍ የሰው ፊት ይመለከት ነበር፥ በሌላውም ወገን ወዳለው የዘንባባ ዛፍ የአንበሳ ፊት ይመለከት ነበር፥ በቤቱ ሁሉ ዙሪያ እንደዚህ ተደርጎ ነበር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 41:19
4 交叉引用  

ልሙጥ በሆነው ነገርም ላይ በአንበሶች፥ በበሬዎችና በኪሩቤል አምሳል የተቀረጹ ምስሎች ነበሩ፤ ከአንበሶቹ፥ ከበሬዎቹና ከኪሩቤሉ ቅርጾች ራስጌና ግርጌ የአበባ ጉንጉን የሚመስሉ ቅርጾች ነበሩ።


የፊታቸውም ምስል የሰው ፊት፥ አራቱም በቀኝ በኩል የአንበሳ ፊት፥ በግራ በኩል የላም ፊት ነበራቸው፥ አራቱም ደግሞ የንስር ፊት ነበራቸው።


እያንዳንዱም አራት አራት ፊት ነበሩት፥ አንደኛው ፊት የኪሩብ ፊት፥ ሁለተኛው ፊት የሰው ፊት፥ ሦስተኛው ፊት የአንበሳ ፊት፥ አራተኛውም ፊት የንስር ፊት ነበረ።


እያንዳንዱ አራት አራት ፊት፥ እያንዳንዱም አራት አራት ክንፍ ነበሩት፥ ከክንፎቻቸው ሥርም የሰው እጅ የሚመስል ነገር ነበረ።


跟着我们:

广告


广告