Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 ወደ ሰሜን የሚመለከተው ቤት መሠዊያውን ለሚጠብቁ ካህናት ነው፤ እነዚህ ከሌዊ ልጆች መካከል እንዲያገለግሉት ወደ ጌታ የሚቀርቡ የሳዶቅ ልጆች ናቸው።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 በሰሜን ትይዩ ያለው ክፍል ደግሞ በመሠዊያው ላይ ለሚያገለግሉ ካህናት ነው። እነዚህም የሳዶቅ ልጆች ሲሆኑ፣ በእግዚአብሔር ፊት ቀርበው ማገልገል የሚችሉ ሌዋውያን እነርሱ ብቻ ናቸው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 ወደ ሰሜን የሚያመለክተውም ክፍል በመሠዊያው ለማገልገል ኃላፊነት ለተሰጣቸው ካህናት ማረፊያ ነው፤ እነዚህ ሁሉ ካህናት ከሳዶቅ ዘር የተወለዱ ሌዋውያን ሲሆኑ፥ በፊቱ ቆመው እግዚአብሔርን ለማገልገል የተፈቀደላቸው እነርሱ ብቻ ናቸው።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 ወደ ሰሜ​ንም የሚ​መ​ለ​ከ​ተው ቤት መሠ​ዊ​ያ​ዉን ለማ​ገ​ል​ገል ለሚ​ተጉ ካህ​ናት ነው፤ እነ​ዚህ ከሌዊ ልጆች መካ​ከል ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ርቡ የሳ​ዶቅ ልጆች ናቸው” አለኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 ወደ ሰሜንም የሚመለከተው ቤት መሠዊያውን ለማገልገል ለሚተጉ ካህናት ነው፥ እነዚህ ከሌዊ ልጆች መካከል ያገለግሉት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ የሳዶቅ ልጆች ናቸው አለኝ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:46
16 交叉引用  

ንጉሥ ሰሎሞን በኢዮአብ ፈንታ በናያን የሠራዊቱ አዛዥ፥ በአብያታርም ፈንታ ሳዶቅን ካህን አድርጎ ሾመ።


ከዚያም ወደ ውጪው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆ በአደባባዩ ዙሪያ የተሠሩ ዕቃ ቤቶችና ወለል ነበሩ፤ በወለሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።


በበሮቹ መተላለፊያ አጠገብ በር ያለው ዕቃ ቤት ነበረ፤ በዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያጥቡ ነበር።


እንዲህም አለኝ፦ በልዩ ስፍራ አንጻር በሰሜንና በደቡብ በኩል ያሉ ዕቃ ቤቶች፥ እነርሱ ወደ ጌታ የሚቀርቡ ካህናት ከሁሉ ይልቅ የተቀደሰውን ምግብ የሚበሉባቸው ቤቶች ናቸው። ስፍራው ቅዱስ ነውና በዚያ የተቀደሰውን ነገር የእህሉን ቁርባን የኃጢአቱንና የበደሉን መሥዋዕት ያኖራሉ።


ሊያገለግሉኝ ወደ እኔ ለሚቀርቡ ለካህናት፥ ከሳዶቅ ዘር ለሆኑ ለሌዋውያን ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትሰጣቸዋለህ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


የእስራኤል ልጆች ከእኔ በራቁ ጊዜ የመቅደሴን ሥርዓት የጠበቁ የሳዶቅ ልጆች ሌዋውያን ካህናት ሊያገለግሉኝ ወደ እኔ ይቀርባሉ፤ ስቡንና ደሙን ወደ እኔ ሊያቀርቡ በፊቴ ይቆማሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ከምድሪቱም የተቀደሰ የዕጣ ክፍል ይሆናል፤ ጌታን ሊያገለግሉ ለሚቀርቡ ለመቅደሱ አገልጋዮች ለካህናቱ ይሆናል፥ ስፍራውም ለቤቶቻቸው መስሪያና ለመቅደስም የሚሆን የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል።


ሌዋውያን በሳቱ ጊዜ፥ እንደ ሳቱት እንደ እስራኤል ልጆች ላልሳቱት ሥርዓቴን ለጠበቁት ከሳዶቅ ልጆች ለተቀደሱት ካህናት ይሆናል።


ሙሴም አሮንን፦ “ጌታ፦ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ እቀደሳለሁ፥ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ’ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ዝም አለ።


“ማናቸውም ሰው ኃጢአትን ቢሠራ፥ በጌታም ላይ ፈጽሞ እምነትን ቢያጎድል፥ በአደራ ከእርሱ ዘንድ የተቀመጠን ነገር ወይም ብድር ወስዶ ባልንጀራውን ቢክድ፥ ወይም ቢቀማ፥ ወይም በባልንጀራው ላይ ግፍ ቢሠራ፥


ተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ ለበደል መሥዋዕት፥ ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ፥ ለጌታ ስለ በደሉ መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያመጣል።


በቆሬና በእርሱም ተከታዮች ላይ የደረሰው እንዳይደርስበት፥ ከአሮን ልጆች ያልሆነ ሌላ ሰው በጌታ ፊት ዕጣንን ለማጠን እንዳይቀርብ፥ ጌታ በሙሴ እንደ ተናገረው፥ ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ አደረጋቸው።


ለቆሬም እርሱንም ለተከሉት ሁሉ እንዲህ ቡሎ ተናገረ፦ “ነገ ጠዋት ጌታ ለእርሱ የሆነውን ሰው፥ ቅዱስም ማን እንሆነ፥ ወደ እርሱም ለመቅረብ የተፈቀደለትን ሰው ያሳውቃል፤ የመረጠውንም ሰው ወደ እርሱ እንዲቀርብ ይፈቅድለታል።


በጭራሽ ዳግመኛ በእስራኤል ልጆች ላይ ቁጣ እንዳይሆንባቸው እናንተ ራሳችሁ የመቅደሱንና የመሠዊያውን ግዴታዎች ፈጽሙ።


አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።


跟着我们:

广告


广告