Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 እንዲህም አለኝ፦ “ይህ ወደ ደቡብ የሚመለከት ቤት ቤቱን ለሚጠብቁ ካህናት ነው፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “በደቡብ ትይዩ ያለው ክፍል በቤተ መቅደስ ውስጥ ለሚያገለግሉ ካህናት ሲሆን፣

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 ያም ሰው እንዲህ አለኝ፦ “ወደ ደቡብ የሚያመለክተው ክፍል በቤተ መቅደሱ ለማገልገል ኀላፊነት ለተሰጣቸው ካህናት ማረፊያ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 ሰው​ዬ​ውም፥ “ይህ ወደ ደቡብ የሚ​መ​ለ​ከት ቤት ለማ​ገ​ል​ገል ለሚ​ተጉ ካህ​ናት ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 ሰውዬውም፦ ይህ ወደ ደቡብ የሚመለከት ቤት ለማገልገል ለሚተጉ ካህናት ነው።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:45
18 交叉引用  

አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአሔር ባርያ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስራኤልም ለማስተስረይ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕጣኑም መሠዊያ ላይ ያጥኑ ነበር።


እነርሱና ልጆቻቸውም በጌታ ቤት በድንኳኑ ደጆች ላይ ዘበኞች ነበሩ።


በየጥዋቱና በየማታውም ለጌታ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና መዓዛው ያማረ ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የተቀደሰውንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹንም ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የጌታን ትእዛዝ እንጠብቃለን፥ እናንተ ግን ትታችሁታል።


የዕርገት መዝሙር። እነሆ፥ ጌታን ባርኩ፥ በአምላካችን ቤት አደባባዮች የምትቆሙ እናንተ የጌታ ባርያዎች ሁላችሁ።


ከዚያም ወደ ውጪው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆ በአደባባዩ ዙሪያ የተሠሩ ዕቃ ቤቶችና ወለል ነበሩ፤ በወለሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።


በበሮቹ መተላለፊያ አጠገብ በር ያለው ዕቃ ቤት ነበረ፤ በዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያጥቡ ነበር።


በመቅደሴ ውስጥ አገልጋዮች፥ በቤቱም በሮች ዘበኞች ይሆናሉ፥ በቤቱም ውስጥ ያገለግላሉ፤ ለሕዝቡም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና መሥዋዕትን ያርዳሉ፥ ሊያገለግሉአቸውም በፊታቸው ይቆማሉ።


የእስራኤል ልጆች ከእኔ በራቁ ጊዜ የመቅደሴን ሥርዓት የጠበቁ የሳዶቅ ልጆች ሌዋውያን ካህናት ሊያገለግሉኝ ወደ እኔ ይቀርባሉ፤ ስቡንና ደሙን ወደ እኔ ሊያቀርቡ በፊቴ ይቆማሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ከምድሪቱም የተቀደሰ የዕጣ ክፍል ይሆናል፤ ጌታን ሊያገለግሉ ለሚቀርቡ ለመቅደሱ አገልጋዮች ለካህናቱ ይሆናል፥ ስፍራውም ለቤቶቻቸው መስሪያና ለመቅደስም የሚሆን የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ዐይኖችህን ወደ ሰሜን መንገድ አንሣ። እኔም ዐይኖቼን ወደ ሰሜን መንገድ አነሣሁ፥ እነሆም በመሠዊያው በር በሰሜን በኩል፥ በመግቢያው የቅናቱ ጣዖት ነበረ።


እንዳትሞቱም የጌታን ትእዛዝ እየጠበቃችሁ፥ ለሰባት ቀን ሌሊትና ቀን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ትቀመጣላችሁ፤ እኔ እንዲህ ታዝዣለሁና።”


በጭራሽ ዳግመኛ በእስራኤል ልጆች ላይ ቁጣ እንዳይሆንባቸው እናንተ ራሳችሁ የመቅደሱንና የመሠዊያውን ግዴታዎች ፈጽሙ።


የሌዋውያንም አለቆች አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ይሆናል፤ እርሱም የመቅደሱን ግዴታ በሚፈጽሙት ላይ ተቆጣጣሪ ይሆናል።


በማደሪያውም ፊት በምሥራቅ በኩል በመገናኛው ድንኳን ፊት በስተ ፀሐይ መውጫ የሚሰፍሩት ሙሴና አሮን ልጆቹም ይሆናሉ፥ በመቅደሱም ውስጥ ማናቸውንም ለእስራኤል ልጆች የሚደረገውን ሥርዓት ይጠብቃሉ፤ ማናቸውም ልዩ ሰው ግን ቢቀርብ ይገደል።


ጢሞቴዎስ ሆይ! በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፤


መንግሥትም፥ ለአባቱም ለእግዚአብሔር ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።


跟着我们:

广告


广告