Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ወደ ደቡብ መራኝ፥ እነሆ ወደ ደቡብ የሚመለከት በር ነበረ፤ የግንቡን አዕማድና መተላለፊያዎቹንም እንደዚያው መጠን አድርጎ ለካ። ከሌሎቹም ጋር እኩል መጠን ነበራቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ከዚያም ወደ ደቡብ አቅጣጫ መራኝ፤ እዚያም ፊቱን ወደ ደቡብ ያደረገ በር አየሁ፤ እርሱም የውስጠኛውን ግድግዳና መተላለፊያ በረንዳውን ለካ፤ የእነዚህም መጠን እንደ ሌሎቹ በሮች ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ከዚያም በኋላ ወደ ደቡብ ወሰደኝ፤ እዚያም በደቡብ በኩል የሚያስወጣ አንድ በር ነበር፤ ሰውየውም የበሩን የግድግዳ ዐምዶችና በስተመጨረሻ ያለውን ክፍል ለካ፤ ስፋታቸውም ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ወደ ደቡ​ብም መራኝ፤ እነ​ሆም ወደ ደቡብ የሚ​መ​ለ​ከት በር ነበረ፤ የግ​ን​ቡን አዕ​ማ​ድና መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹ​ንም እን​ደ​ዚ​ያው መጠን አድ​ርጎ ለካ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ወደ ደቡብም መራኝ፥ እነሆም፥ ወደ ደቡብ የሚመለከት በር ነበረ፥ የግንቡን አዕማድና መዛነቢያዎቹንም እንደዚያው መጠን አድርጎ ለካ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:24
6 交叉引用  

ጓዳዎቹ፥ የግንቡ አዕማድና መተላለፊያዎቹ ከሌሎቹ ጋር እኩል መጠን ነበራቸው፤ በእርሱና በመተላለፊያዎቹ ዙሪያ መስኮቶች ነበሩ፤ ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱ ደግሞ ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።


ፊቱ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በር መጣ፥ በደረጃዎቹም ወጥቶ በበሩ በኩል ያለውን የቤቱን መግቢያ ወለል ወርዱን ለካ አንድ ዘንግ ነበር፥ የሌላኛውም የቤቱ መግቢያ ወለል ወርድ አንድ ዘንግ ነበር።


የምድሪቱ ሕዝብ ግን በየክብረ በዓሉ ቀን ወደ ጌታ ፊት በመጡ ጊዜ በሰሜን በር በኩል ሊሰግድ የገባው በደቡብ በር በኩል ይውጣ፥ በደቡብ በር የገባው በሰሜን በር በኩል ይውጣ፤ በፊት ለፊት ባለው ይውጣ እንጂ በገባበት በር አይመለስ።


跟着我们:

广告


广告