Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የምሥራቁ በር ጓዳዎች በዚህ በኩል ሦስት በዚያ በኩል ደግሞ ሦስት ነበሩ፥ ሦስቱም እኩል ስፋት ነበራቸው፤ የግንቡም አዕማድ ወርድ በዚህ በኩልና በዚያ በኩል እኩል ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በምሥራቁ በር ግራና ቀኝ መጠናቸው እኩል የሆነ ሦስት ሦስት የዘብ ቤቶች ነበሩ፤ በመካከላቸው ወጣ ወጣ ብለው የሚታዩትም ግንቦች ተመሳሳይና እኩል ነበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እነዚህም የዘብ ማረፊያ ክፍሎች ከመተላለፊያው በስተጐን እያንዳንዳቸው ተመሳሳይ ስፋት ነበራቸው፤ በእነርሱ መካከል ያሉትም ግንቦች ሁሉ ተመሳሳይ ውፍረት ነበራቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የም​ሥ​ራ​ቁም ዕቃ ቤቶች በዚህ በኩል ሦስት፥ በዚ​ያም በኩል ሦስት፥ ነበሩ፤ ለሦ​ስ​ቱም አንድ ልክ ነበረ፤ የግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ወርድ በዚህ በኩ​ልና በዚያ በኩል አንድ ልክ ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የምሥራቁም በር የዘበኛ ጓዳዎች በዚህ በኩል ሦስት በዚያም በኩል ሦስት ነበሩ፥ ለሦስቱም አንድ ልክ ነበረ፥ የግንቡም አዕማድ ወርድ በዚህ በኩልና በዚያ በኩል አንድ ልክ ነበረ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:10
6 交叉引用  

የበሩን መግቢያ ወርድ ዐሥር ክንድ፥ የበሩን ርዝመት ዐሥራ ሦስት ክንድ አድርጎ ለካ።


ጓዳዎቹም በዚህ በኩል ሦስት በዚያም በኩል ሦስት ነበሩ፤ የግንቡ አዕማድና መተላለፊያዎቹ እንደ ፊተኛው በር መጠናቸው እኩል ነበር፤ ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበር።


ጓዳዎቹ፥ የግንቡ አዕማድና መተላለፊያዎቹ ከሌሎቹ ጋር እኩል መጠን ነበራቸው፤ በእርሱና በመተላለፊያዎቹ ዙሪያ መስኮቶች ነበሩ፤ ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱ ደግሞ ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።


በውስጠኛው መግቢያ በውጭው በኩል በውስጠኛው አደባባይ ለሚዘምሩ ዕቃ ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚመለከት በር አጠገብ ነበረ፥ ወደ ደቡብም ይመለከት ነበር፤ ሌላው ደግሞ ወደ ምሥራቅ በሚመለከተው በር አጠገብ ነበረ፥ ወደ ሰሜን ይመለከት ነበር።


ክፍሉም ርዝመቱ አንድ ዘንግ፥ ወርዱም አንድ ዘንግ ነበረ፤ በክፍሎቹ መካከል ያለው ርቀት አምስት ክንድ ነበረ፤ ከበራፉም በውስጥ በኩል የሚገኝ የበሩ መተላለፊያ ወለል አንድ ዘንግ ነበረ።


የበሩን መተላለፊያ ስምንት ክንድ፥ የግንቡንም አዕማድ ሁለት ክንድ አድርጎ ለካ፤ የበሩም መተላለፊያ በውስጥ በኩል ነበረ።


跟着我们:

广告


广告