ሕዝቅኤል 4:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 እኔም እንዲህ አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወይኔ! እነሆ፥ ሰውነቴ አልረከሰችም፥ ከልጅነቴ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ፥ የሞተ ወይም እንስሳ የገደለውን ከቶ አልበላሁም፥ ርኩስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አልገባም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ወይኔ! ከቶ ረክሼ አላውቅም፤ ከልጅነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ጥንብ ወይም አውሬ የጣለውን በልቼ አላውቅም፤ ርኩስ ሥጋም በአፌ አልገባም” አልሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 እኔም እንዲህ ስል መለስኩ፦ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ይህስ ከቶ አይሁን! እኔ ከቶ ረክሼ አላውቅም፤ ከሕፃንነቴ ጀምሮ የበከተ ወይም አውሬ የገደለው ከብትን ሥጋ የበላሁበት ጊዜ የለም፤ ጸያፍ ምግብም አልበላሁም።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እኔም፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ይህ አግባብ አይደለም፤ እነሆ ሰውነቴ አልረከሰችም፤ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ጥንብና አውሬ የሰበረውን ከቶ አልበላሁም፤ ርኵስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አልገባም” አልሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እኔም፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! እነሆ፥ ሰውነቴ አልረከሰችም፥ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ጥንብና አውሬ የሰበረውን ከቶ አልበላሁም፥ ርኩስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አልገባም አልሁ። 参见章节 |