Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 38:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በተራሮቼ ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁ፥ የሰውም ሁሉ ሰይፍ በወንድሙ ላይ ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በተራሮቼም ሁሉ በጎግ ላይ ሰይፍ እጠራለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእያንዳንዱም ሰው ሰይፍ በወንድሙ ላይ ያርፋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በተራሮቼ ሁሉ በጎግ ላይ ሰይፍ እንዲመዘዝ አደርጋለሁ፤ የያንዳንዱም ሰው ሰይፍ ጓደኛውን ይበላል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በተ​ራ​ሮ​ችም ሁሉ በእ​ርሱ ላይ ፍር​ሀ​ትን እጠ​ራ​ለሁ፤ የሰ​ውም ሁሉ ሰይፍ በወ​ን​ድሙ ላይ ይሆ​ናል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በተራሮቼም ሁሉ በእርሱ ላይ ሰይፍን እጠራለሁ፥ የሰውም ሁሉ ሰይፍ በወንድሙ ላይ ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 38:21
9 交叉引用  

የአሞንና የሞዓብም ልጆችም በሴይርም ተራራ በሚኖሩት ላይ ፈጽመው ሊገድሉአቸውና ሊያጠፉአቸውም ተነሥተውባቸው ነበር፤ በሴይርም የሚኖሩትን ካጠፉ በኋላ አንዱ ሌላውን በማገዝ እርስ በርስ ተጠፋፉ።


በምድር ላይ ራብን ጠራ፥ የእህልን ኃይል ሁሉ ሰበረ።


ጌታም በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በእሳትና በሰይፉ ይፈርዳል፤ በጌታም ተወግተው የሞቱት ይበዛሉ።


እነሆ፥ ስሜ የተጠራባት ከተማ ላይ ክፉን ነገር ማምጣት እጀምራለሁ፤ በውኑ እናንተ ፈጽሞ ያልተቀጣችሁ ትሆናላችሁን? በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁና ያለ ቅጣት አትቀሩም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ በላቸው።


ወይም በዚያች ምድር ላይ ሰይፍ አምጥቼ፦ በምድሪቱ ላይ ሰይፍ ይለፍ ብል፥ ሰውንና እንስሳን ከእርሷ ባጠፋ፥


የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለሁ፥ የአሕዛብ መንግሥታትን ኃይል አጠፋለሁ፤ ሰረገሎችንና ነጂዎቻቸውን እገለብጣለሁ፤ ፈረሶችንና ፈረሰኞቻቸው እያንዳንዱ በወንድሙ ሰይፍ ይወድቃሉ።


በዚያም ቀን ከእግዚአብሔር የመጣ ታላቅ ሽብር በእነርሱ ላይ ያድራል፤ እርስ በእርሳቸውም ይያያዛሉ፥ አንዱም በሌላው ላይ ይነሣል።


የሦስት መቶው ቀንደ መለከት ድምፅ እንደተሰማም ጌታ በሰፈሩ ውስጥ ያለው ሰው አንዱ በሌላው ላይ ሰይፉን እንዲመዝበት አደረገ፤ ሠራዊቱ በጽሬራ አቅጣጫ እስከ ቤትሺጣ፥ ከዚያም አልፈው በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልመሖላ ድንበር ድረስ ሸሽተው ሄዱ።


ከዚያም ሳኦልና ሰዎቹ ተሰብስበው ወደ ውጊያው ሄዱ። እዚያም ፍልስጥኤማውያን ግራ በመጋባት በታላቅ ትርምስ እርስ በርሳቸው በሰይፍ ይጋደሉ ነበር።


跟着我们:

广告


广告