Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 38:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የባሕር ዓሣዎች፥ የሰማይ ወፎች፥ የምድር አራዊት፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በፊቴ ይንቀጠቀጣሉ፥ ተራሮች ይገለባበጣሉ፥ ገደሎች ይወድቃሉ፥ ቅጥርም ሁሉ ወደ ምድር ይወድቃል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 የባሕር ዓሦች፣ የሰማይ ወፎች፣ የምድር አራዊት፣ በምድር ላይ የሚሳብ ፍጡር ሁሉ፣ እንዲሁም በምድር ላይ ያለ ሰው ሁሉ፣ በፊቴ ይንቀጠቀጣሉ፤ ተራሮች ይገለባበጣሉ፤ ገደሎች ይናዳሉ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እያንዳንዱ የዓሣና የወፍ ዐይነት፥ እያንዳንዱም አውሬና እንስሳ በምድር የሚኖር እያንዳንዱ ሰው እኔን በመፍራቱ ይንቀጠቀጣል፤ ተራራዎች ይወድቃሉ፤ ገደሎች ተፈረካክሰው ይናዳሉ፤ እያንዳንዱም የቅጽር ግንብ ይደረመሳል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት የተ​ነሣ የባ​ሕር ዓሣ​ዎ​ችና የሰ​ማይ ወፎች፥ የም​ድረ በዳም አራ​ዊት፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ሁሉ፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ኖሩ ሰዎች ሁሉ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ተራ​ሮ​ችም ይገ​ለ​ባ​በ​ጣሉ፤ ገዳ​ላ​ገ​ደ​ሎ​ችም ይወ​ድ​ቃሉ፤ ቅጥ​ርም ሁሉ ወደ ምድር ይወ​ድ​ቃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ከፊቴም የተነሣ የባሕር ዓሣዎችና የሰማይ ወፎች የምድረ በዳም አራዊት በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ በምድርም ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ፥ ተራሮችም ይገለባበጣሉ ገደላገደሎችም ይወድቃሉ ቅጥርም ሁሉ ወደ ምድር ይወድቃል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 38:20
9 交叉引用  

በታላቅም እልቂት ቀን ግንቦች በወደቁ ጊዜ በረጅሙ ተራራ ሁሉ፥ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ፥ ወንዞችና የውኃ ፈሳሾች ይወርዳሉ።


ተራሮችንና ኮረብቶችን አፈርሳለሁ፥ ቡቃያዎቻቸውንም ሁሉ አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ደሴቶች አደርጋለሁ፥ ኩሬዎችንም አደርቃለሁ።


ስለዚህ ምድሪቱ ታለቅሳለች፥ በእርሷም የሚቀመጡ ሁሉ ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች ጋር በድካም ይዝላሉ፤ የባሕሩም ዓሦች እንኳ ያልቃሉ።


ምክንያቱም የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለም፤ ምሽግን ለመስበር መለኮታዊ ኃይል አለው።


ሰማይም እንደ መጽሐፍ ተጠቅልሎ አለፈ፤ ተራራዎችና ደሴቶችም ሁሉ ከስፍራቸው ተወገዱ።


跟着我们:

广告


广告