Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 38:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእነርሱ ላይ እንደማመጣህ፥ ለብዙ ዓመት በተነበዩ በአገልጋዮቼ በእስራኤል ነቢያት እጅ በቀደመው ዘመን ስለ እርሱ የተናገርሁ አንተ ነህን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በቀደመው ዘመን በባሪያዎቼ በእስራኤል ነቢያት ስለ እርሱ የተናገርሁለት ያ ሰው አንተ አይደለህምን? በዚያ ወቅት አንተን በእነርሱ ላይ እንደማመጣባቸው ለብዙ ዓመታት ትንቢት ተናገሩ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አንተን እንደማመጣ አገልጋዮቼ የእስራኤል ነቢያት በቀድሞ ዘመን በመደጋገም ትንቢት ተናግረዋል።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጎግ እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ነ​ርሱ ላይ እን​ደ​ማ​መ​ጣህ፥ በዚ​ያች ዘመን ብዙ ዓመት ትን​ቢት በተ​ና​ገሩ በባ​ሪ​ያ​ዎች በእ​ስ​ራ​ኤል ነቢ​ያት እጅ በቀ​ደ​መው ዘመን ስለ እርሱ የተ​ና​ገ​ርሁ አንተ ነህን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእነርሱ ላይ እንደማመጣህ በዚያች ዘመን ብዙ ዓመት ትንቢት በተናገሩ በባሪያዎቼ በእስራኤል ነቢያቶች በቀደመው ዘመን ስለ እርሱ የተናገርሁ አንተ ነህን?

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 38:17
13 交叉引用  

በዚያም ቀን ጌታ ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን፥ የሚጠቀለለውንም እባብ ሌዋታንን፥ በጠንካራ በታላቅ፥ በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፤ በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድላል።


ከሩቅ ያሉትን ሕዝቦች የሚጠራበትን ምልክት ያቆማል፤ ከምድር ዳርቻም በፉጨት ይጠራቸዋል፤ እነርሱም እየተጣደፉ በፍጥነት ይመጣሉ።


ምድርን እንደሚሸፍን ደመና በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ትወጣለህ። ጎግ ሆይ፥ በአንተ በኩል ቅድስናዬን በፊታቸው በምገልጥበት ጊዜ፥ አሕዛብ እንዲያውቁኝ፥ በኋለኛው ዘመን በምድሬ ላይ አመጣሃለሁ።


አሁንም፦ “ትርከስ፥ ዓይናችን በጽዮን ላይ ይሁን” የሚሉ ብዙ አሕዛብ በአንቺ ላይ ተሰብስበዋል።


跟着我们:

广告


广告