Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 38:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሳባ፥ ድዳን፥ የተርሴስ ነጋዴዎች፥ መንገዶችዋም ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ ምርኮን ትማርክ ዘንድ መጥተሃልን? ብዝበዛንስ ትበዘብዝ ዘንድ ብርንና ወርቅንስ ትወስድ ዘንድ ከብትንና ዕቃንስ ትወስድ ዘንድ እጅግስ ብዙ ምርኮ ትማርክ ዘንድ ወገንህን ሰብስበሃልን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሳባና ድዳን፣ የተርሴስ ነጋዴዎችና መንደሮቿም ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፤ “ልትዘርፍ መጣህን? ሰራዊትህን ያሰባሰብኸው ለመበዝበዝ፣ ወርቅና ብሩን አጋብሶ ለመሄድ፣ ከብቱንና ሸቀጡን ለመውሰድ፣ ብዙ ምርኮ ይዞ ለመመለስ ነውን?” ’

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሳባና ዴዳን፥ እንዲሁም የተርሴስ ነጋዴዎችና ወጣት ጦረኞች እንዲህ ይሉሃል፦ ‘ምርኮን ለመውሰድ መጣህን? ብርንና ወርቅን፥ እንስሶችና ቈሳቊስን፥ ማለት ብዙ ምርኮን እንዲያጓጒዙልህ ብዛት ያላቸውን ሰዎችህን ሰበሰብክን?’ ”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሳባና ድዳን፥ የተ​ር​ሴ​ስም ነጋ​ዴ​ዎች፥ መን​ደ​ሮ​ች​ዋም ሁሉ፦ ምር​ኮን ትማ​ርክ ዘንድ መጥ​ተ​ሃ​ልን? ብዝ​በ​ዛ​ንስ ትበ​ዘ​ብዝ ዘንድ፥ ብር​ንና ወር​ቅ​ንስ ትወ​ስድ ዘንድ፥ ከብ​ት​ንና ዕቃ​ንስ ትወ​ስድ ዘንድ፥ እጅ​ግስ ብዙ ምርኮ ትማ​ርክ ዘንድ ወገ​ን​ህን ሰብ​ስ​በ​ሃ​ልን? ይሉ​ሃል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሳባና ድዳን የተርሴስም ነጋዴዎች መንገዶችዋም ሁሉ፦ ምርኮን ትማርክ ዘንድ መጥተሃልን? ብዝበዛንስ ትበዘብዝ ዘንድ ብርንና ወርቅንስ ትወስድ ዘንድ ከብትንና ዕቃንስ ትወስድ ዘንድ እጅግስ ብዙ ምርኮ ትማርክ ዘንድ ወገንህን ሰብስበሃልን? ይሉሃል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 38:13
17 交叉引用  

ከሰማይ ልኮ አዳነኝ፥ ለረገጡኝም ውርደትን ሰጣቸው፥ እግዚአብሔር ቸርነቱንና እውነቱን ላከ።


ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፤ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፤ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፤ በሚያስቆጣኝም ሕዝብ ላይ እሰደዋለሁ።


ገመዶችህ ላልተዋል፥ ችካላቸውንም አልጸናም፥ ሸራውንም መወጠር አልቻሉም። በዚያን ጊዜ የብዙ ምርኮ ሀብት ይከፋፈላል፤ አንካሶች እንኳ ከክፍፍሉ ይደርሳቸዋል።


“በመላ ግዛቶችህ ውስጥ ስላለ ኃጢአትህ ሁሉ ባለጠግነትህንና መዝገብህን ለብዝበዛ በከንቱ አሳልፌ እሰጣለሁ።


እስራኤል የባዘነ በግ ነው፤ አንበሶች አሳደዱት፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።


በአንድነትም እንደ አንበሶች ያገሣሉ፥ እንደ አንበሳም ደቦሎች ያጉረመርማሉ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኤዶምያስ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፥ ከእርሷም ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከቴማን ጀምሮ እስከ ድዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።


ከሀብትሽ ብዛት የተነሣ ተርሴስ ነጋዴሽ ነበረች፥ በብርና በብረት በቆርቆሮና በእርሳስ ዕቃሽን ለወጡ።


የድዳን ልጆችም ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ይለውጡ ዘንድ የዝሆን ጥርስና ዞጲ አመጡልሽ።


ድዳን ለግልቢያ በሚሆን ኮርቻ ነጋዴሽ ነበረች።


የተርሴስ መርከቦች ሸቀጥሽን የሚያጓጉዙልሽ ነበሩ፤ አንቺም ተሞልተሽ ነበር፥ በባሕርም ልብ ውስጥ እጅግ ከበርሽ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፥ እንዲህም በለው፦ በሕዝቦች መካከል አንበሳ መሰልህ፥ እንደ ባሕር አውሬ ነበርህ፤ በወንዞችህም ገንፍለህ ወጥተሃል፥ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም አሳድፈሃል።


ጌታ ተናግሮአልና ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን በይሁዳ ልጆች እጅ እሸጣለሁ፥ እነርሱም ለሩቆቹ ሕዝብ ለሳባ ሰዎች ይሸጡአችኋል።


የእረኞች ክብር ተዋርዶአልና የዋይታቸውን ድምፅ ስሙ! የዮርዳኖስ ጥቅጥቅ ደን ወድሟልና የአንበሶች ግሣት ድምፅ ስሙ!


跟着我们:

广告


广告