ሕዝቅኤል 36:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)35 “ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆነች፤ የወደሙት፥ ባድማ የሆኑት፥ የፈረሱት ከተሞች አጥር ተሰርቶላቸዋል፥ መኖሪያም ሆነዋል” ይላሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም35 እነርሱም፣ “ጠፍ የነበረው ይህ ምድር እንደ ዔድን ገነት መሰለ፤ የተደመሰሱ፣ የፈራረሱና ባድማ የሆኑት ከተሞች አሁን መኖሪያና ምሽግ ሆነዋል” ይላሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም35 ተመልካችም ሁሉ ‘ጭራሽ ምድረ በዳ ሆና የነበረች ይህች ምድር እንዴት የዔደንን ገነት መሰለች! ቀድሞ ባድማ ወናና የፍርስራሽ ክምር ሆነው የነበሩትስ ከተሞች እንዴት እንደገና ሕዝብ ሊኖርባቸውና የተመሸጉ ሊሆኑ ቻሉ?’ ይላሉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)35 ሰዎችም ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆናለች፤ የፈረሱት፥ ባድማ የሆኑት፥ የጠፉትም ከተሞች ተመሽገዋል፤ ሰውም የሚኖርባቸው ሆነዋል ይላሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)35 ሰዎችም፦ ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆናለች፥ የፈረሱት ባድማ የሆኑት የጠፉትም ከተሞች ተመሽገዋል ሰውም የሚኖርባቸው ሆነዋል ይላሉ። 参见章节 |