Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 33:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እርሱም በምድሪቷ ላይ ሰይፍ ሲመጣ አይቶ መለከትን ቢነፋ ሕዝቡንም ቢያስጠነቅቅ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እርሱም በምድሪቱ ላይ ሰይፍ ሲመጣ አይቶ፣ ሕዝቡን ለማስጠንቀቅ መለከት ቢነፋ፣

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ጠባቂውም ጠላት ሲመጣ ቢያይና ከአደጋ መጠንቀቅ የሚያስችል የመለከት ድምፅ ለሰዎች ሁሉ ቢያሰማ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እር​ሱም በም​ድር ላይ የመ​ጣ​ውን ጦር በአየ ጊዜ መለ​ከ​ትን ቢነፋ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ቢያ​ስ​ጠ​ነ​ቅቅ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እርሱም በምድር ላይ የመጣውን ሰይፍ ባየ ጊዜ መለከትን ቢነፋ ሕዝቡንም ቢያስጠነቅቅ፥

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 33:3
12 交叉引用  

በኃይልህ ጩኽ፥ አትቈጥብ፥ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፥ ለሕዝቤ መተላለፋቸውን ለያዕቆብ ቤትም ኃጢአታቸውን ንገር።


በይሁዳ ላይ ተናገሩ በኢየሩሳሌምም ላይ አውጁ፦ “በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ በሉ፤ ጮኻችሁም፦ ‘ሁላችሁ ተሰብሰቡ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ’ በሉ።


በምድር ላይ ዓላማን አንሡ በአሕዛብም መካከል መለከት ንፉ፥ አሕዛብንም ለጦርነት በእርሷ ላይ አዘጋጁ፤ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት ጥሩባት አለቃንም በእርሷ ላይ ሹሙ፤ እንደ ጠጉራም ኩብኩባ ፈረሶችን በእርሷ ላይ አውጡ።


እናንተ የብንያም ልጆች ሆይ! ክፉ ነገር ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ይጐበኛልና ከኢየሩሳሌም ውስጥ ለደህንነታችሁ ሽሹ፥ በቴቁሔ መለከቱን ንፉ፥ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት አንሡ።


ነገር ግን አንተ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው፥ እርሱም ከኃጢአቱና ከክፉ መንገዱ ባይመለስ፥ እርሱ በኃጢአቱ ይሞታል፥ አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።


መለከትን ወደ አፍህ አቅርብ፤ ቃል ኪዳኔን ተላልፈዋልና፥ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና እንደ ንስር በጌታ ቤት ላይ እያንዣበበ ነው።


የጌታ ቀን መጥቷልና፥ እርሱም ቀርቧልና በጽዮን መለከትን ንፉ፥ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ እሪ በሉ፥ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ።


ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ቢነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? ወይስ ጌታ ካላደረገው በቀር በከተማ ላይ ክፉ ነገር ይሆናልን?


ደግሞም መለከት ትክክል ያልሆነ የጥሪ ድምፅ ካሰማ፥ ለጦርነት ማን ይዘጋጃል?


跟着我们:

广告


广告