Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 33:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 በሰሩትም ርኩሰት ሁሉ ምድሪቱን ባድማና ውድማ በማደርግበት ጊዜ፥ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ካደረጓቸው አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ የተነሣ፤ ምድሪቱን ጠፍና ባድማ በማደርግበት ጊዜ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እነርሱ በፈጸሙአቸው አጸያፊ ነገሮች ሁሉ ምክንያት ምድሪቱን ባድማና ወና በማደርግበት ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ስላ​ደ​ረ​ጉ​ትም ርኵ​ሰት ሁሉ ምድ​ሪ​ቱን ባድ​ማና ውድማ ባደ​ረ​ግሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ስላደረጉትም ርኩሰት ሁሉ ምድሪቱን ባድማና ውድማ ባደርግሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 33:29
26 交叉引用  

አሕዛብ በሠሩት ጉድጓድ ወደቁ፥ በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደች።


ግብፃውያንም በፈርዖንና በሰረገሎቹ በፈረሰኞቹም ላይ ክብር ባገኘሁ ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።”


ምድራቸውን ለመሣቀቂያና ለዘለዓለም ማፍዋጫ አድርገዋል፤ የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፥ ራሱንም ይነቀንቃል።


ፊቴን በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፥ ከእሳት ቢያመልጡም፥ እሳት ግን ይበላቸዋል፥ ፊቴን በእነርሱ ላይ ባደረግሁ ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


እምነተ ቢስ ሆነዋልና ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


አመንዝራነታችሁን በላያችሁ ላይ ይመልሳሉ፥ የጣዖቶቻችሁን ኃጢአት ትሸከማላችሁ፥ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


በሞዓብም ላይ ፍርድ እሰጣለሁ። እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ምድሪቱን ባድማና ውድማ አደርጋታለሁ፥ የኃይልዋም ትዕቢት ይቀራል፥ የእስራኤልም ተራሮች ማንም እንዳያልፍባቸው ባድማ ይሆናሉ።


አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ የሕዝብህ ልጆች በቅጥር አጠገብና በቤቶቻቸው ደጃፍ ስለ አንተ ይናገራሉ፥ አንዱ ከአንዱ ጋር፥ እያንዳንዱ ከወንድሙ ጋር እንዲህ ይላሉ፦ ኑ ከጌታ የመጣው ቃል ምን እንደሆነ እንስማ።


ይህም በመጣም ጊዜ፥ እነሆ ይመጣል! ነቢይ በመካከላቸው እንደ ነበረ ያውቃሉ።


ስለ ርኩሰትሽ ሁሉ እስከ አሁን ያላደረግኹትን፥ ከዚህ በኋላም እርሱን የሚመስል የማላደርገውን ነገር በአንቺ ላይ አደርግብሻለሁ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእጅህ አጨብጭብ፥ በእግርህም እየረገጥህ፥ ስለ የእስራኤል ቤት ክፉ የርኩሰት ሥራዎቻቸው ሁሉ ወዮ! በል፤ በሰይፍ፥ በራብና በቸነፈር ይወድቃሉና፤


የተገደሉትም በመካከላችሁ ይወድቃሉ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


ንጉሡ ያለቅሳል፥ ልዑሉም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድሪቱም ሕዝቦች እጆች ይንቀጠቀጣሉ፥ እንደ መንገዳቸው መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ዓይኔ አይራራልሽም እኔም አላዝንም፤ መንገድሽን በአንቺ ላይ እመልስብሻለሁ፥ ርኩሰቶችሽም በመካከልሽ ይሆናሉ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


跟着我们:

广告


广告