ሕዝቅኤል 32:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ሜሼክና ቱባል ብዛታቸውም ሁሉ በዚያ አሉ መቃብራቸውም በዙሪያቸው ነው፤ በሕያዋን ምድር ያሸብሩ ስለ ነበር ሁሉም ያልተገረዙ ሲሆኑ በሰይፍ ተገድለዋል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም26 “ሜሼኽና ቶቤል መቃብሮቻቸው በብዙ ሰራዊታቸው መቃብር ተከብበው ይገኛሉ፤ ሁሉም ያልተገረዙ ሲሆኑ፣ በሕያዋን ምድር ሽብራቸውን ስለ ነዙ በሰይፍ ተገድለዋል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 “የሜሼክና የቱባል ወታደሮች ሕዝቦቻቸው መቃብሮች በዚያ ነበሩ፤ እነርሱ የተገደሉት በጦርነት ነው፤ ሁሉም በእግዚአብሔር ያላመኑ ናቸው፤ ይሁን እንጂ እነርሱም ከዚህ በፊት የሕያዋንን ዓለም የሚያሸብሩ ነበሩ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 “ሞሳሕና ቶቤል፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በዚያ አሉ፤ መቃብራቸውም በዙሪያቸው ነው፤ ሁሉም ሳይገረዙ በሰይፍ ተገድለዋል፤ በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ነበርና። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ሞሳሕና ቶቤል ብዛታቸውም ሁሉ በዚያ አሉ መቃብራቸውም በዙሪያቸው ነው፥ ሁሉም ሳይገረዙ በሰይፍ ተገድለዋል፥ በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ነበርና። 参见章节 |