Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 31:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በሕዝቦች መካከል በጥላው የኖሩ ክንዱ ወደነበሩት፥ በሰይፍ ወደ ተገደሉት ከእርሱ ጋር ወደ ሲኦል ወረዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከአሕዛብ መካከል ከርሱ ጋራ ያበሩ፣ በጥላው ሥር የኖሩ፣ በሰይፍ ከሞቱት ጋራ ለመቀላቀል ወደ መቃብር ወርደዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በጥላው ሥር የነበሩትና ከሕዝቦች መካከል ተባባሪዎቹ የነበሩት በሰይፍ ወደ ተገደሉት ከእርሱ ጋር ወደ ሙታን ዓለም ይወርዳሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እነ​ር​ሱም በሰ​ይፍ ወደ ተገ​ደ​ሉት ወደ ሲኦል ከእ​ርሱ ጋር ወረዱ፤ በጥ​ላው ሥር ይኖሩ የነ​በሩ ዘሮ​ቹም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ጠፉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ክንዱም ወደ ነበሩት በአሕዛብም መካከል በጥላው ወደ ተቀመጡት፥ በሰይፍ ወደ ተገደሉት ሰዎች ወደ ሲኦል ከእርሱ ጋር ወረዱ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 31:17
12 交叉引用  

ጌታ ተገለጠ፥ ፍርድንም አከናወነ፥ ክፉ በገዛ እጆቹ ሥራ ተጠመደ።


ሲኦል በመምጣትህ ልትገናኝህ በታች ታወከች፤ የሞቱትንም፥ የምድርንም ታላላቆች ሁሉ፥ ለአንተ አንቀሳቀሰች፥ የአሕዛብንም ነገሥታት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው አስነሣች።


ሬስ። ስለ እርሱ፦ በአሕዛብ መካከል በጥላው በሕይወት እንኖራለን ያልነው በእግዚአብሔር የተቀባ፥ የሕይወታችን እስትንፋስ፥ በጉድጓዳቸው ተያዘ።


ባዕዳን፥ የሕዝቦች ጨካኞች የሆኑ፥ ቆርጠው ጣሉት፤ በተራሮች እና በሸለቆዎች ሁሉ ውስጥ ቅርጫፎቹ ወደቁ፥ ቅርንጫፎቹም በምድር ፈሳሾች ሁሉ ላይ ተሰባበሩ፥ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከጥላው ወጥተው ትተውት ሄዱ።


እነሆ አሦር ቅርጫፉ የተዋበ፥ ጥላ የሚሰጥ ጫካ፥ ቁመቱ የረዘመ፥ ጫፉም በቅርንጫፎች መካከል የነበረ የሊባኖስ ዝግባ ነበረ።


የሰማይ ወፎች ሁሉ ጎጆአቸውን በቅርንጫፎቹ ላይ ሠሩ፥ የምድር አራዊት ሁሉ ከቅርጫፎቹ በታች ወለዱ፥ ታላላቅ ሕዝቦች ሁሉ ከጥላው በታች ኖሩ።


በተዘራችም ጊዜ ትወጣለች፤ ከአትክልትም ሁሉ የምትበልጥ ትሆናለች፤ የሰማይ ወፎችም በጥላዋ ሊሰፍሩ እስኪችሉ ታላላቅ ቅርንጫፎች ታወጣለች።”


跟着我们:

广告


广告