Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 30:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በዚያ ቀን ያለ ስጋት የተቀመጠችውን ኢትዮጵያን ለማስፈራራት መልእክተኞች ከፊቴ በመርከብ ይወጣሉ፤ እንደ ግብጽም ቀን ጭንቀት ይሆንባቸዋል፤ እነሆ መጥቷልና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ ‘በዚያ ቀን ከእኔ ዘንድ መልእክተኞች በመርከብ ወጥተው ያለ ሥጋት ከተቀመጠችበት ሁኔታ ለማውጣት ኢትዮጵያን ያስፈራሯታል፤ ግብጽ በጨለማ በምትዋጥበት ቀን ጭንቅ ይይዛቸዋል፤ ቀኑ በርግጥ ይመጣልና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በዚያን ቀን ‘አንዳች ነገር ይደርስብናል’ ብለው ያልተጠራጠሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማስፈራራት መልእክተኞች በእኔ ትእዛዝ ይወጣሉ፤ እነርሱም በግብጽ ላይ በእርግጥ በሚመጣው ጥፋት ምክንያት ይጨነቃሉ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በዚያ ቀን መል​እ​ክ​ተ​ኞች ተዘ​ል​ለው የሚ​ኖ​ሩ​ትን ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንን ለማ​ጥ​ፋት ከፊቴ በመ​ር​ከብ ይወ​ጣሉ፤ በግ​ብ​ፅም ቀን ሁከት ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ እነሆ፥ ይመ​ጣ​ልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በዚያ ቀን መልእክተኞች ተዘልለው የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማስፈራት ከፊቴ በመርከብ ይወጣሉ፥ እንደ ግብጽም ቀን ሁከት ይሆንባቸዋል፥ እነሆ፥ ይመጣልና።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 30:9
24 交叉引用  

የይሁዳም ምድር ለግብጽ ሽብር ትሆናለች፤ የሠራዊት ጌታ ከመከረባት ምክር የተነሣ ወሬዋን የሚሰማ ሁሉ ይፈራል።


ጌታም እንዲህ አለ፦ “አገልጋዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት እንዲሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፥


እነርሱም ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ ከትምክሕታቸውም ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ፤ ያፍራሉም።


ከጢሮስ የሚመጣው ዜና፤ በግብጽ በሚሰማበት ጊዜ ጭንቅ ይይዛቸዋል።


አሁንም አንቺ ተድላን የምትወጅ፥ በምቾትም የምትቀመጪ፥ በልብሽም፦ “እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበለትም ሆኜ አልኖርም፥ የወላድ መካንነትንም አላውቅም” የምትዪ ይህን ስሚ፤


ከመውደቃቸው ድምፅ የተነሣ ምድር ተናወጠች፥ የጩኸትም ድምፅ በኤርትራ ባሕር ተሰማ።


“ተነሡ፥ በደኅንነት ተቀምጦ ተረጋግቶ ወዳለው፥ የቅጥር በርና መቀርቀሪያ ወደሌለው ብቻውንም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ ውጡ፥ ይላል ጌታ።


እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ፤ ይፈፀማል፥ እኔም አደርገዋለሁ፤ አልቆጠብም፥ አልራራም፥ አልጸጸትም። እንደ መንገድሽና እንደ ሥራሽ ይፈርዱብሻል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


በዚያን ጊዜ የባሕር አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውን ያስቀምጣሉ፥ ወርቀዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ፤ መንቀጥቀጥን ይለብሳሉ፥ በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ፥ በአንቺም ይደነቃሉ።


በደሴቶች የሚኖሩ ሁሉ በአንቺ ደንግጠዋል፥ ነገሥታቶቻቸውም እጅግ ፈርተዋል፥ ፊታቸውም ተለውጦአል።


ይህም በመጣም ጊዜ፥ እነሆ ይመጣል! ነቢይ በመካከላቸው እንደ ነበረ ያውቃሉ።


እንዲህም ትላለህ፦ ቅጥር ወደሌላቸው መንደሮች እወጣለሁ፤ ያለ ሥጋት በሰላም ወደሚኖሩ፥ ሁሉም ሳይፈሩ ያለ ቅጥር፥ ያለ መወርወሪያና ያለ በር ወደሚቀመጡ እሄዳለሁ፤


በማጎግ እና ያለ ስጋት በደሴቶች በሚቀመጡት ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፤ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ጌታ እግዚአብሔር፦ እናንተን በሜንጦ፥ ትሩፋቶቻችሁንም በመንጠቆ የሚወስዱበት ቀን፥ እነሆ፥ በላያችሁ ይመጣል ብሎ በቅዱስነቱ ምሎአል።


ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይፈጥናል፥ እርሱም አይዋሽም፤ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ጠብቀው፤ አይዘገይም።


እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ።


ስጋት ሳይኖርባት የተቀመጠች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፥ በልብዋም፦ “እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ያለች፥ እንዴት አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ ሆነች! በእርሷ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፏጫል።


የጌታ ቀን ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥ እንዲሁ የሚመጣ መሆኑን እናንተው ራሳችሁ በጥንቃቄ አውቃችኋልና።


ስለዚህ አምስቱ ሰዎች ከዚያ ተነሥተው ወደ ላይሽ መጡ፤ ሲዶናውያን ያለ ስጋት በጸጥታ እንደሚኖሩ ሁሉ፥ በዚያም የሚኖረው ሕዝብ በሰላም እንደሚኖር አዩ። ምድሪቱ አንዳች የሚጐድላት ነገር ባለ መኖሩ ሕዝቡ ባለጸጋ ነበር። እንዲሁም ከሲዶናውያን ርቆ የሚኖር ሲሆን፥ ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ግንኙነት አልነበረውም።


跟着我们:

广告


广告