ሕዝቅኤል 30:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 በዚያ የግብጽን ቀንበር በምሰብርበት ጊዜ፥ በትሐፍንሔስ ቀኑ ይጨልማል፥ የኃይልዋ ትዕቢት በውስጧ ይጠፋል፤ ደመናም ይጋርዳታል፥ ሴቶች ልጆችዋም ተማርከው ይወሰዳሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም18 የግብጽን ቀንበር በምሰብርበት ጊዜ፣ በጣፍናስ ቀኑ ይጨልማል፤ ከዚያም የተኵራራችበት ብርታት ይንኰታኰታል። በደመና ትሸፈናለች፤ መንደሮቿም ይማረካሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 የግብጽን ኀይል በመሰባበር የሚመኩበትን ብርታት በማስወግድበት ጊዜ ጣፍናስ በጨለማ ትጋረዳለች፤ ግብጽ በደመና ትሸፈናለች፤ የከተሞችዋ ኗሪዎችም ተማርከው ይወሰዳሉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 የግብፅን ቀንበር በዚያ በሰበርሁ ጊዜ በጣፍናስ ቀኑ ይጨልማል፤ የኀይልዋም ትዕቢት ይጠፋባታል፤ ደመናም ይጋርዳታል፤ ሴቶች ልጆችዋም ይማረካሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 የግብጽን ቀንበር በዚያ በሰበርሁ ጊዜ በጣፍናስ ቀኑ ይጨልማል የኃይልዋም ትዕቢት ይጠፋባታል፥ ደመናም ይጋርዳታል፥ ሴቶች ልጆችዋም ይማረካሉ። 参见章节 |