Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 30:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ወንዞችን አደርቃለሁ፥ ምድሪቱን በክፉ ሰዎች እጅ እሸጣለሁ፥ ምድሪቱንና ሞላዋን በባዕዳን እጅ ባድማ አደርጋለሁ፤ እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የአባይን ወንዝ ውሃ አደርቃለሁ፤ ምድሪቱን ለክፉ ሰዎች እሸጣለሁ፤ በባዕዳን እጅ፣ ምድሪቷንና በውስጧ ያለውን ሁሉ ባድማ አደርጋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የዓባይን ወንዝ ውሃ አደርቃለሁ፤ ግብጽም በክፉ ሰዎች ሥልጣን ሥር እንድትወድቅ አደርጋለሁ። ስለዚህም ባዕዳን ሕዝብ አገሪቱን በሞላ ያጠፋሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ወን​ዞ​ች​ንም ምድረ በዳ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም በክፉ ሰዎች እጅ እሰ​ጣ​ለሁ፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንና ሞላ​ዋ​ንም በባ​ዕ​ዳን እጅ ባድማ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋለሁ ምድሪቱንም በክፉ ሰዎች እጅ እሸጣለሁ፥ ምድሪቱንና ሙላዋንም በእንግዶች እጅ ባድማ አደርጋለሁ፥ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬያለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 30:12
12 交叉引用  

ቀላዩም፦ “ደረቅ ሁን፥ ፈሳሾችህንም አደርቃለሁ” እላለሁ፤


እርሷ የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናትና፥ እነርሱም በጣዖታቱ ላይ እንደ እብድ ይሆናሉና ድርቅ በውኆችዋ ላይ ይሆናል እነርሱም ይደርቃሉ።


ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሙግትሽን እምዋገትልሻለሁ በቀልሽንም እበቀልልሻለሁ፤ ባሕርዋንም አደርቀዋለሁ ምንጭዋንም እንዲደርቅ አደርጋለሁ።


በባዕዳን እጅ ያልተገረዙትን ሰዎች ሞት ትሞታለህ፤ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


እንዲህም ብለህ ተናገር፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “‘ወንዙ የእኔ ነው እኔ ራሴ ሠርቼዋለሁ’ የምትል፥ በወንዞች መካከል የምትተኛ፥ አንተ ታላቅ ድራጎን የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ፥ እነሆ በአንተ ላይ ነኝ።


ባዕዳን፥ የሕዝቦች ጨካኞች የሆኑ፥ ቆርጠው ጣሉት፤ በተራሮች እና በሸለቆዎች ሁሉ ውስጥ ቅርጫፎቹ ወደቁ፥ ቅርንጫፎቹም በምድር ፈሳሾች ሁሉ ላይ ተሰባበሩ፥ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከጥላው ወጥተው ትተውት ሄዱ።


ባሕሩንም ይገሥጻል፥ ያደርቀዋልም፥ ወንዞችን ሁሉ ያደርቃል፤ ባሳንና ቀርሜሎስም ጠውልጎአል፥ የሊባኖስም አበባ ጠውልጎአል።


ምድር የጌታ ነውና፥ በእርሷ የሞላባት ሁሉ።


ስድስተኛውም መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውሃው ደረቀ።


ስለዚህ ጌታ በእስራኤል ላይ በመቈጣቱ ለሚዘርፏቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ በዙሪያቸው ላሉ ጠላቶቻቸው ሸጣቸው።


跟着我们:

广告


广告