Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 30:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እርሱና ከሕዝቦች ሁሉ ርህራሄ የሌላቸው ሕዝቡ ምድሪቱን ለማጥፋት ይመጣሉ፤ ሰይፋቸውንም በግብጽ ላይ ይመዝዛሉ ምድሪቱንም በሬሳ ይሞላሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከአሕዛብ ሁሉ እጅግ ጨካኝ የሆኑት፣ እርሱና ሰራዊቱ፣ ምድሪቱን ለማጥፋት እንዲመጡ ይደረጋል፤ ሰይፋቸውን በግብጽ ላይ ይመዝዛሉ፤ ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋሉ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እርሱም ምሕረት የሌለውን ጨካኝ ሠራዊቱን አስከትሎ ምድሪቱን ለመደምሰስ ይመጣል። እነርሱም ግብጽን በሰይፍ ይመታሉ። አገሪቱም በሬሳ የተሞላች ትሆናለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እር​ሱና ሕዝቡ የአ​ሕ​ዛ​ብም ኀያ​ላን ምድ​ሪ​ቱን ለማ​ጥ​ፋት ይላ​ካሉ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም በሰ​ይፍ ይወ​ጉ​አ​ቸ​ዋል፤ ምድ​ሪ​ቱም በሙ​ታን ትሞ​ላ​ለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እርሱና የአሕዛብ ጨካኞች ሕዝቡ ምድሪቱን ለማጥፋት ይመጣሉ፥ ሰይፋቸውንም በግብጽ ላይ ይመዝዛሉ ምድሪቱንም በተገደሉት ይሞላሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 30:11
14 交叉引用  

ስለዚህ እነሆ ባዕዳንን፥ ጨካኞች መንግሥታትን አመጣብሃለሁ፤ በጥበብህ ውበት ላይ ሰይፋቸውን ይመዝዛሉ፥ ድምቀትህን ያረክሳሉ።


የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ ሰይፌንም በእጁ አኖራለሁ፤ የፈርዖንንም ክንድ እሰብራለሁ፥ እሱም በፊቱ ክፉኛ እንደቆሰለ ሰው ያቃስታል።


ለሕዝቦች መሪ እጅ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እርሱም እንደ ክፉቱ መጠን ያደረግበታል እኔም አባርረዋለሁ።


ባዕዳን፥ የሕዝቦች ጨካኞች የሆኑ፥ ቆርጠው ጣሉት፤ በተራሮች እና በሸለቆዎች ሁሉ ውስጥ ቅርጫፎቹ ወደቁ፥ ቅርንጫፎቹም በምድር ፈሳሾች ሁሉ ላይ ተሰባበሩ፥ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከጥላው ወጥተው ትተውት ሄዱ።


በኃያላን ሰይፍ ብዙ ሕዝብህን እጥላለሁ፤ ከአሕዛብ ሁሉ ጨካኞች ናቸው፤ የግበጽንም ትዕቢት ያወድማሉ ብዛትዋም ሁሉ ይጠፋል።


ተራሮቹንም በተገደሉት ሰዎች እሞላለሁ፤ በኮረብቶችህ፥ በሸለቆዎችህና በውሃ መውረጃዎችህ ሁሉ ላይ በሰይፍ የተገደሉት ይወድቃሉ።


አንተ፥ ወታደሮችህና ከአንተም ጋር ያሉ ሕዝብ ሁሉ በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ፤ ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።


እርሱም ሽማግሌ የማያከብርና ለብላቴና የማይራራ፥ ሲያዩት የሚያስፈራ ሕዝብ ነው።


跟着我们:

广告


广告