Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 3:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ይህም የሕያዋኑ ክንፎች እርስ በእርሳቸው ሲማቱ የሚወጣው ድምፅ፥ በአጠገባቸውም የነበሩት የመንኰራኵሮች ድምፅ ነበር፥ እርሱም ታላቅ የሚያጉረመርም ድምፅ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ይህም የሕያዋኑ ፍጡራን ክንፎች እርስ በርስ ሲጋጩና በአጠገባቸው ያሉት መንኰራኵሮች የሚያሰሙት ታላቅ ህምህምታ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የሕያዋን ፍጥረቶቹ ክንፎቹ እርስ በርሳቸው በአየር ላይ ሲፋጩ ሰማሁ፤ ከመንኰራኲሮቹም የሚሰማው የጋጋታ ድምፅ ከፍተኛ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የእ​ነ​ዚ​ያም እን​ስሳ ክን​ፎች እርስ በር​ሳ​ቸው ሲማቱ፥ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ችን ድምፅ፥ የታ​ላ​ቁ​ንም ንው​ጽ​ው​ጽታ ድምፅ ሰማሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የአራቱም እንስሳ ክንፎች እርስ በርሳቸው ሲማቱ፥ በአጠገባቸውም የመንኰራኵሮችን ድምፅ፥ የጽኑውንም ንውጥውጥታ ድምፅ ሰማሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 3:13
6 交叉引用  

በሾላው ዛፎች ጫፍ ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማም፥ ጌታ የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ለመምታት ቀድሞህ ወጥቶአል ማለት ነውና በዚያን ጊዜ ፍጠን።”


እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ከነሐስ የተሠሩ አራት መንኰራኲሮችና መንኰራኲሮቹ የሚሽከረከሩበት የነሐስ ወስከምቶች ነበራቸው፤ እንዲሁም በአራቱ ማእዘኖች የመታጠቢያ ገንዳ መደገፊያዎች ነበሩ፤ መደገፊያዎቹም የአበባ ጉንጉን በሚመስሉ ቅርጾች አጊጠው ነበር።


ሕያዋኑንም ስመለከት፥ እነሆ፥ በአራቱ ሕያዋን አጠገብ በምድር ላይ ለእያንዳንዳቸው አንድ አንድ መንኰራኵር አየሁ።


ሲሄዱም የክንፎቻቸውን ድምፅ እንደ ብዙ ውኆች ድምፅ፥ እንደ ሁሉን የሚችል አምላክ ድምፅ፥ እንደ ማዕበል ድምፅ፥ እንደ የታላቅ ሠራዊት ድምፅ ሆኖ ሰማሁ፤ ሲቆሙም ክንፎቻቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር።


ሁሉን የሚችል አምላክ ሲናገር እንደሚያሰማው ዓይነት ድምፅ የኪሩቤል ክንፎች ድምፅ እስከ ውጭው አደባባይ ድረስ ተሰማ።


跟着我们:

广告


广告