Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 28:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በበደልህ ብዛት በንግድህም ኃጢአት መቅደስህን አረከሰህ፤ ስለዚህ እሳትን ከውስጥህ አውጥቻለሁ እርሷም በልታሃለች፥ በሚያዩህም ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አድርጌሃለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በኀጢአትህና በተጭበረበረው ንግድህ ብዛት፣ መቅደስህን አረከስህ። ስለዚህ እሳት ከአንተ እንዲወጣ አደረግሁ፤ እርሱም በላህ፤ በሚመለከቱህ ሁሉ ፊት፣ በምድር ላይ ዐመድ አደረግሁህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በመግዛትና በመሸጥ ከፈጸምከው በደል የተነሣ የአምልኮ ስፍራዎችህ ሁሉ ረከሱ፤ ስለዚህ በከተማይቱ የሰደድ እሳት እንዲነሣ አድርጌ በሙሉ አቃጠልኳት፤ አሁን ወደ አንተ የሚመለከቱ ሁሉ ዐመድ ብቻ መሆንክን ያያሉ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በበ​ደ​ልህ ብዛት፥ በን​ግ​ድ​ህም ኀጢ​አት መቅ​ደ​ስ​ህን አረ​ከ​ስህ፤ ስለ​ዚህ እሳ​ትን ከው​ስ​ጥህ አው​ጥ​ቻ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋም በል​ታ​ሃ​ለች፤ በሚ​ያ​ዩ​ህም ሁሉ ፊት በም​ድር ላይ አመድ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በበደልህ ብዛት በንግድህም ኃጢአት መቅደስህን አረከሰህ፥ ስለዚህ እሳትን ከውስጥህ አውጥቻለሁ እርስዋም በልታሃለች፥ በሚያዩህም ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አድርጌሃለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 28:18
17 交叉引用  

ጌታም በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በእሳትና በሰይፉ ይፈርዳል፤ በጌታም ተወግተው የሞቱት ይበዛሉ።


ከተፈጠርህበት ቀን ጀምረህ በደል እስኪገኝብህ ድረስ በመንገድህ ፍጹም ነበርህ።


በንግድህ ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ ኃጢአትንም ሠራህ፤ ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፤ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፥ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ የጢሮስን ገዥ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርቶአል አንተም እንዲህ ብለሃል፦ እኔ አምላክ ነኝ፥ በእግዚአብሔር ወንበር በባሕር ልብ ተቀምጫለሁ፤ ነገር ግን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።


ከእነዚህም እንደገና ወስደህ በእሳት ውስጥ ትጥላቸዋለህ፥ በእሳትም ታቃጥላቸዋለህ፥ ከእርሱም እሳት ወደ እስራኤል ቤት ሁሉ ትወጣለች።


በረባት ቅጥር ላይ እሳትን አነዳለሁ፤ በጦርነትም ቀን በጩኸት፥ በዐውሎ ነፋስም ቀን በሁከት የእርሷን የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፤


በሞዓብ ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የቂርዮትንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፤ ሞዓብም በውካታና በጩኸት በመለከትም ድምፅ መካከል ይሞታል፤


በይሁዳ ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች።”


እነሆ፥ ጌታ ሀብቷን ይገፍፋታል፥ ወደ ባሕርም ውስጥ ያሰምጠዋል፤ እርሷም በእሳት ትበላለች።


እኔ በምሠራበት ቀን ክፉዎችን ትረግጧቸዋላችሁ፥ ከእግራችሁ ጫማ በታች አመድ ይሆናሉና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


ሰው ዓለሙ ሁሉ የእርሱ ቢሆንና ነፍሱን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል?


ኃጢአትንም እያደረጉ ላሉት ምሳሌ እንዲሆን፤ የሰዶምንና ገሞራን ከተማዎች አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ እንዲጠፉ ከፈረደባቸው፥


ስለዚህም ሞትና ኀዘን፥ ራብም የሆኑት መቅሰፍቶችዋ በአንድ ቀን ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።”


የእሾኽ ቊጥቋጦውም ዛፎቹን፥ “በእርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾ ቊጥቋጦው ይነሣ፤ የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ” አላቸው።


ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቤሜሌክ ትውጣና እናንተን፥ የሴኬምንና የቤትሚሎን ነዋሪዎች ትብላ፤ እንዲሁም እሳት ከእናንተ፥ ከሴኬምና ከቤትሚሎን ነዋሪዎች ትውጣና አቤሜሌክን ትብላ።”


跟着我们:

广告


广告