Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 27:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ከሕዝቦች መካከል ያሉ ነጋዴዎች አፏጩብሽ፤ አስደንጋጭ ሆነሻል፥ ለዘለዓለምም አትገኚም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 በሌሎች ሕዝቦች መካከል ያሉ ነጋዴዎች ምንኛ አፏጩብሽ! መጨረሻሽ አስደንጋጭ ሆነ፤ ለዘላለምም አትገኚም።’ ”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 እነሆ የሕዝቦች ነጋዴዎች ያላግጡብሻል። መጨረሻሽ አስደንጋጭ ሆኖአል፤ ለዘለዓለምም አትገኚም።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 የአ​ሕ​ዛብ ነጋ​ዴ​ዎ​ችም አፍ​ዋ​ጩ​ብሽ፤ አን​ቺም ፈጽ​መሽ ትጠ​ፊ​ያ​ለሽ፤ ከእ​ግ​ዲ​ህም ወዲያ እስከ ዘለ​ዓ​ለም አት​ኖ​ሪም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 የአሕዛብ ነጋዴዎች አፍዋጩብሽ፥ አንቺ ለድንጋጤ ሆነሻል፥ እስከ ዘላለምም አትገኚም።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 27:36
14 交叉引用  

ይህ ከፍ ከፍ ብሎ የሚታየው ቤተ መቅደስ ፈርሶ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ በኩል የሚያልፉ ሰዎች ይህን አይተው በመደንገጥ ‘እግዚአብሔር ይህን አገርና ይህን ቤተ መቅደስ ለምን እንዲህ አደረገ?’ በማለት ይሳለቁበታል።


ጥቂት ጊዜ ቆይቶ፥ ክፉ አድራጊ አይኖርም፥ ትፈልገዋለህ ቦታውንም አታገኝም።


ብመለስ ግን አጣሁት፥ ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም።


ምድራቸውን ለመሣቀቂያና ለዘለዓለም ማፍዋጫ አድርገዋል፤ የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፥ ራሱንም ይነቀንቃል።


ይህችንም ከተማ ለመሣቀቂና ለማፍዋጫ አደርጋታለሁ፤ የሚያልፍባትም ሁሉ ይሣቀቃል፥ ስለ ተደረገባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጭባታል።


“ኤዶምያስም መሣቀቂያ ትሆናለች፥ የሚያልፍባትም ሁሉ ይሣቀቃል፥ ስለ ተደረገባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጭባታል።


ከጌታ ቁጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ ሰው አይቀመጥባትም፤ በባቢሎንም በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይሣቀቃል በመጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጫል።


ሳምኬት። መንገድ አላፊዎች ሁሉ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻልና፦ በውኑ የውበት ፍጻሜና የምድር ሁሉ ደስታ የሚሉአት ከተማ ይህች ናትን? እያሉ፥ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍዋጫሉ፥ ራሳቸውንም ያነቃንቃሉ።


የተራቆተ ዓለት አደርግሻለሁ፤ የመረብ ማስጫ ትሆኛለሽ፤ ዳግምም አትሠሪም፤ እኔ ጌታ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


የሰው ልጅ ሆይ ጢሮስ በኢየሩሳሌም ላይ፦ “እሰይ የሕዝቦች በር የነበረች ተሰበረች፤ ወደ እኔም ተመለሰች፤ እርሷ ስለፈረሰች እኔ እሞላለሁ፤” ብላለችና።


ለድንጋጤ አደርግሻለሁ፥ እንግዲህም አትኖሪም፤ ትፈለጊአለሽ ለዘለዓለምም አትገኚም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


በአሕዛብም ውስጥ የሚያውቁህ ሁሉ ይደነቁብሃል፤ አንተ ለድንጋጤ ሆነሃል፥ እስከ ዘለዓለምም አትገኝም።


ስጋት ሳይኖርባት የተቀመጠች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፥ በልብዋም፦ “እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ያለች፥ እንዴት አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ ሆነች! በእርሷ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፏጫል።


跟着我们:

广告


广告