Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 27:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ሸቀጥሽ ከባሕር በወጣ ጊዜ ብዙ ሕዝቦችን አጥግበሻል፤ በተትረፈረፈ በሀብትሽና በሸቀጣ ሸቀጥሽ የምድርን ነገሥታት አበልጽገሻል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ሸቀጥሽ ከባሕር በወጣ ጊዜ፤ ብዙ ሕዝቦችን ታጠግቢ ነበር፣ በታላቅ ሀብትሽና ሸቀጥሽ፣ የምድርን ነገሥታት ታበለጥጊ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 የሸቀጥ ዕቃሽ በየሀገሩ ሲሠራጭ፥ የየሀገሩን ሕዝብ ፍላጎት ያሟላ ነበር፤ ከአንቺ በተትረፈረፈ ሀብትና ሸቀጥ የምድር ነገሥታትን አበልጽገሻል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 በባ​ሕር ውስጥ ምን ያህል ዋጋ ታገኚ ነበር? በብ​ል​ጥ​ግ​ናሽ ብዛት ብዙ አሕ​ዛ​ብን አጠ​ገ​ብሽ፤ ከአ​ን​ቺም ጋር አንድ ከሆ​ኑት ለይ​ተሽ የም​ድ​ርን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ባለ​ጸ​ጎች አደ​ረ​ግ​ሻ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ሸቀጥሽ ከባሕር በወጣ ጊዜ ብዙ አሕዛብን አጥግበሻል፥ በብልጥግናሽና በንግድሽ ብዛት የምድርን ነገሥታት ባለ ጠጎች አድርገሻል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 27:33
9 交叉引用  

በባሕር መግቢያ ለምትኖረውና፥ በብዙ ደሴቶች ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር ለምትነግደው ጢሮስ እንዲህ በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ፥ አንቺ፦ “በውበት ፍጹም ነኝ” ብለሻል።


በንግድህ ብዛት ግፍ በውስጥህ ተሞላ ኃጢአትንም ሠራህ፤ ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ፤ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፥ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ።


ጢሮስም ምሽግን ለራስዋ ሠርታለች፥ ብሩንም እንደ አፈር ወርቁንም እንደ መንገድ ጭቃ አከማችታለች።


በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ “በባሕር መርከቦች ያሉአቸውን ሁሉ ከሀብቷ የተነሣ ሀብታም ላደረገች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! በአንድ ሰዓት ጠፍታለችና፤” እያሉ ጮኹ።


አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቁጣ ወይን ጠጅ ጠጥተዋልና፤ የምድርም ነገሥታት ከእርሷ ጋር ሴስነዋልና፤ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኃይል የተነሣ ሀብታሞች ሆነዋልና፤” ብሎ ጮኸ።


跟着我们:

广告


广告